በትግራይ ክልል፣ ሰሜን ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች የተበላሸ ፣መጥፎ ጠረን ያለው እና የነቀዘ ዱቄት ከለጋሽ ደርጅቶች መታደላቸውን ገልጸዋል።

22/05/16

ላለፉት 13 ወራት የረባ ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁት ተፈናቃዮቹ ፤ ከረጅም ጊዚያት በኃላ ጥር 20/2016 ዓ.ም መሰጠት የተጀመረው ዱቄት ጥራት የሌለው ፣ የተበላሽ ፣ የነቀዘና መጥፎ ጥረን ያለው መሆኑ በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። 

የቴሌቪዥን ጣቢያው ” ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው ዱቄት ለምግብነት ቢያውሉት ለጤናቸው ጠንቅ እንደሚሆን የምግብ ባለሙያዎች አረጋግጠውልኛል ” ብሏል።  

ዱቄቱ በእርዳታ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች ‘ተበላሸ’ ስለተባለው እህል ምላሽ እንዲሰጡ የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

ጉዳዩ በጥብቅ እየተከታተለው መሆኑ የገለፀው የእንዳስላሰ ሽረ መንግስታዊ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ፤  ዱቄቱ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች ያደሉት እንዲሰበስቡና ማደል እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ መፃፉን አስታውቋል።

ፅህፈት ቤቱ ለለጋሽ ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ በመጋዝን የተከማቸውና ለተፈናቃዮች የታደለው ዱቄት ተዘዋውሮ መመልከቱንና የተበላሸ መሆኑ ማረጋገጡ ገልጿል።