አዲስ ዜና

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን በጥብቅ እንደምትቃወም የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናገሩ፡፡

09/05/2016 የአረብ ሊግ በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ ነው፤  ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓለም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል። የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሊጉ መግለጫ፥ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለውታል፡፡ አክለው  ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት ሆኖም የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ነው ብለዋል፡፡ የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ ባካሄደው የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያና…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአሜሪካው የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ  ማይክ ሐመር  ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የአሜሪካው የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ  ማይክ ሐመር  ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

09/05/2016 የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር  ወደ ካምፓላ እና አዲስ አበባ ይጓዛሉ ብሏል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በመግለጫው ። አምባሳደር ሐመር በካምፓላ ፤ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ላይ በሚያተኩረው 42ኛው የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል። አምባሳደር ሐመር ከካምፓላ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ ገልጿል።በኡጋንዳ መዲና ዛሬ የሚካሄደው የኢጋድ ስብሰባ ከያዛቸው ሁለት መወያያ ርዕሶች አንደኛው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው።ኢጋድ ይህን በተመለከተ ውይይት ለማድረግ ስብሰባ መጥራቱን ያወደሰችው አሜሪካ ተወካይዋ አምባሳደር ሐመር…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአብሮነት ትስስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተጨማሪ እርምጃዎች እና መግለጫዎች እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአብሮነት ትስስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተጨማሪ እርምጃዎች እና መግለጫዎች እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ

09/05/2016 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት ትናንት ጥር 8/2016 ዓም  በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ስላለው ሁኔታ ለመመካከር ስብሰባ አካሂዶ ነበር። የስብሰባው መርሐ ግብር ቀደም ተብሎ የተያዘ አልነበረም፡፡በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በሶማሊያ እና ኢትዮበሁለቱ ሃገራት  መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት ስብሰባውን ማድረግ እንዳስፈለገ ምክርቤቱ ተናግሯል፡፡ የሶማሊያ ባለስልጣናት የሀገራቸውን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ወደ ጦርነት ለመግባት ያላቸውን ቁርጠኝነት ካስታወቁ በኋላ ሶማሊያ በጉዳዩ ላይ ስብሰባ እንዲጠሩ ለአፍሪካ ህብረት እና ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት (UNSC) ጥያቄ መላኳ ተሰምቶ ነበር። ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱ ሀገራቱ  ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ ከሚለው ስጋት በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠራ 

የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠራ 

ጥር 08/2016 በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሊመክር እንደሆነ በአፍሪካ ህብረት እና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናት እና ምርምር የሚያደርገው “አማኒ አፍሪካ”    አስነብቧል፡፡በስብሰባው ላይ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማብራሪያ እንደሚያቀርቡ  ይጠበቃል፡፡ ስብሰባውን በንግግር የሚከፍቱት የዚህ ወር የምክር ቤቱ ሊቀመንበር የሆኑት፤ በአፍሪካ ህብረት የጋና አምባሳደር አማ ቱም-አሙሃ ናቸው።  እርሳቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴዎዬ፤ ጉዳዩን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ገለጻ እንደሚሰጡ “አማኒ አፍሪካ” አስታውቋል። በአፍሪካ ግጭቶችን የመከላከል እና ከተከሰቱም በኋላ የመቆጣጠርና መፍትሄ የማበጀት ዓላማ ያለው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት 15 አባል…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን፣ ኢጋድ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብቷል በማለት ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ዛሬ አስታውቃለች። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነችው ጅቡቲ አቻቸው በጻፉት ደብዳቤ፣ ይህንኑ ውሳኔ አሳውቀዋል። ሱዳን ከኢጋድ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ በመጭው ሐሙስ ኡጋንዳ ላይ የተጠራው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባዔ ወታደራዊውን መንግሥት ሳያማክር የሱዳኑን ጦርነት አጀንዳው ማድረጉንና የፈጥኖ ደራሹን ኃይል እንዲገኙ መጋበዛቸውን በመቃወም ነው። የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በኢጋድ ጉባኤ ላይ እንደማይገኙ ከትናንት ወዲያ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢጋድ አስቸኳዩን የመሪዎች ጉባኤ የጠራው፣ በሱዳኑ ጦርነት ዙሪያ ለመወያየትና የኢትዮጵያና ሱማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን ለማብረድ ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ
ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ኢትዮጵያዊያን የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት የዲጂታል መታወቂያን ግዴታ ወደ መሆን ሊሸጋገር እንደደሆነ  የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ዳይሬክተር ዮዳሔ ዘሚካኤል ተናግረዋል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኩል በተለያዩ ምዕራፎች ይተገበራል ከተባለው የምዘገባ ሂደት በኋላ  ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት እንደሚታገዱ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡  ዳይሬክተሩ፣ ተቋማት ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ደንበኞቻቸውን አገልግሎት የመንፈግ ሕጋዊ መብት አላቸው ማለታቸውም ተገልጧል። እስከ አሁን አገልግሎቱን ለማግኘት አራት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 መታወቂያ ለማግኘት ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸውን ሁሉንም ዜጎች ለመመዝገብ ተይዞ የነበረው ቀነ-ገደብ ወደ 2028  ተሸጋግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን በሻሸጎ ፣ ሶሮና ምዕራብ ሶሮ ወረዳዎች በሴቶች ላይ በሚፈጸም ግርዛት ዙሪያ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል። በሻሸጎ ወረዳ በማኅበረሰቡ ዘንድ ‘ጨበላ’ በመባል የሚታወቅ የተደጋጋሚ ግርዛት ጎጂ ልማድ በአካባቢው በበጋ ወራት በሁሉም ዕድሜ ክልል በሚገኙ ሴቶች ላይ በስፋት እንደሚፈጸም እንዲሁም ሴቶችና ሴት ሕፃናት መራቢያ አካላቸው አካባቢ ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እንደመፍትሔ የሚወሰድ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ጎጂ ልማድ የሚያልፉ ሴቶች ከጤና እክል ጀምሮ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት የሚደርስባቸው መሆኑ በክትትሉ ከተለዩ ግኝቶቹ መካከል መሆኑን ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ተጎጂዎች ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እየተሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አጥጋቢ አለመሆን ሴቶች…
ተጨማሪ ያንብቡ
አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የአሜሪካ መከላከያ ኃይልና የኢምባሲው የጸጥታ ትብብር ቢሮ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማጽዳት እያደረገች ያለውን ዘመቻ ለማገዝ ከኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ተቋም ጋር የጋራ ፕሮጀክት መጀመራቸውን  አስታውቋል። ኢምባሲው፣ ኢትዮጵያ ፈንጂዎችን ለማጽዳት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ፣ ፔንታጎን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በትብብር የሚሠሩ ባለሙያዎችን መላኩን ገልጧል።የቡድኑ አባላት ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እና ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም የተውጣጡ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ  ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የዳሰሳ ጥናቱን እና ቀጣይ ድጋፎችን በተመለከተም  የኤምባሲው ተወካዮች እና የባለሙያዎች ቡድኑ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎች ጋር   ጥር 6፤ 2016…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም!

መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም!

እናት ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም ሲል አሳሰበ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተክርስቲያን ክብረ በዓላት የቤተክርስቲያኒቷን ዶግማ፣ ቀኖናና ሥርዓት ጠብቀው እንዳይከወኑ የሚያደርጉ መንግሥታዊ ጫናዎች ተበራክተዋል ያለው ፓርቲው እንዲህ ያለው ተጽዕኖ ካረፈባቸው በዓላት ውስጥ የጥምቀት ክብረ በዓል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው ብሏል። ይህንኑም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት "የጥምቀት በዓል አከባበርን እና ወቅታዊ ጉዳዮችን" መሠረት አድርጎ ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከተሰጠው መግለጫ ፓርቲያችን ለመረዳት ችሏል ብሏል በመግለጫው። በዓሉ የአለም ቅርስ እንደመሆኑ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በክብረ በዓሉ የሚሳተፉ ምዕመናንና ጎብኚዎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ ለበዓሉ ስኬታማነት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የከተሞች የልምድ ልውውጥ አውደጥናት መድረኮች በከተማ ልማት ዘርፍ ዙሪያ የሚታዩ መልካም አፈጻጸሞችና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል

የከተሞች የልምድ ልውውጥ አውደጥናት መድረኮች በከተማ ልማት ዘርፍ ዙሪያ የሚታዩ መልካም አፈጻጸሞችና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል

(ጥር 04 ቀን፣ 2016 ዓ.ም፣ ድሬዳዋ) የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚስቴር ጋር በመተባበር በማዘጋጃቤታዊ ገቢ ሪፎርም፣ በከተማ ፕላን አፈጻጸም፣ በመሬት አስተዳደር፣ ህጋዊ ካዳስተርና ጽዳትና ውበት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹና በዕቅድ የሚመሩ እንዲሁም የነዋሪዎቻቸውን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይሩ ለማድረግ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ  እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ፈንታ አያይዘው እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ከመሰረቱ ቀደምት ሃገራት መካከል አንዷ እንደመሆኗ መጠን…
ተጨማሪ ያንብቡ