አዲስ ጊዜ

227 Posts
የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ::

የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ::

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ  “የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል” ብሏል። ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው “ጽንፈኛ” ባላቸው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል። የኢትዮጵያ ባህር ሀይል የባህር ሃይል ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እንደተሰማሩ እና ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም አዛዡ መናገራቸው ተገልጿል። የባህር ሃይል ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል እንደሆነም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ ተናግረዋል ተብሏል። የባህር ሃይል ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ::

በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ::

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱንአዲ ጊዜ  ከወጣው  የጨረታ ሰነድ ተመልክታለች። የሊዝ ጨረታው በከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ላ የወጣ ጨረታ የለም፡፡ የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ም ተመልክተኛል፡፡ በኮሪደር ልማት በፈረሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም አካባቢ 22 ቦታዎች ለሊዝ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ፡፡

ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 29 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ልዩነት መፍታት እንዳልቻለች ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ልዩነት መፍታት እንዳልቻለች ተገለጸ

በዋሸንግተን በሚካሄደው የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ እየተካፈለች ትገኛለች፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት የጠየቀች ሲሆን ተቋሙ ግን ብድር ለኢትዮጵያ ከመስጠቱ በፊት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡ከተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ኢትዮጵያ የብሯን የመግዛት አቅም እንድታዳክም የሚለው ሲሆን ይህ ጉዳይ እስካሁን አጨቃጫቂ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ድርድር ሲያደርጉ ከአንድ ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን በየጊዜው ሳይስማሙ በመለያየት ላይ ናቸው፡፡ከአንድ ወር በፊት የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለ15…
ተጨማሪ ያንብቡ
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን ቢቢሲ በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን ቢቢሲ በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ  በምርመራ ማረጋገጡን ዘግቧል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮችም በፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች ትዕዛዝ በተለይም የመንግሥትን ገፅታ በሰው ሰራሽ መንገድ ለመገንባት ፌስቡክ ላይ በሚደረጉ አሳሳች ዘመቻዎች ላይ እንደሚሳተፉም ተናግሯል፡፡ ቢቢሲ ለዚህ ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አመራር፣ የፓርቲ አባል እንዲሁም በከተማዋ እና በፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች  አነጋግሬያለሁ ያለ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት  ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ፡፡

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የፖለቲካ ውጥረት በተፈጠረ ቁጥር ጋዜጠኞችን ማሠር እንዲያቆሙ  ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጸጥታ ኃይሎች ስምንት ጋዜጠኞችን እንዳሠሩ ገልጦ፣ እስር ቤት በሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ ደሞ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ብሏል። የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና ከሁለት ወራት በፊት የታሠረው የሱማሌ ክልሉ ጋዜጠኛ ሙሂያዲን ሞሃመድ ባስቸኳይ እንዲፈቱና በገነት ላይ ተፈጽሟል የተባለው ጥቃትም እንዲጣራ ሲፒጄ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የራያ አለላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

የራያ አለላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

ከተማዋ በመከላከያ እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ወድቃለች እታገኘሁ መኮነን የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሃይሉ አበራ ተናግረዋል፡፡ ከተማዋም ከሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም. ጀምሮ  በመከላከያ ሠራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መግባቷ ተሰምቷል፡፡ አቶ ሃይሉ የአቶ ሞላ ህልፈትከትግራይ ኃይሎች ጋር በተደረገ “ውጊያ” አይደለም ብለዋል፡፡ በህግ የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ ምክንያቱን ለመግለጽ ፍቃደኛ አይደለሁም ብለዋል፡፡ የከተማዋ  ነዋሪዎች ከሰኞ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ ነዋሪዎች ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሄዳቸውን ተናግረዋል። አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ወደ ቆቦ ከተማ መግባታቸውም ተሰምቷል፡፡ የራያ አላማጣ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የአማራ ታጣቂዎች” ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል ተናገረ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የአማራ ታጣቂዎች” ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል ተናገረ

በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ታደሰ ወረደ ተናገሩ። አቶ ታደሰ  “የመጀመሪያው እርምጃ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችን ማፍረስ እና የተቋቋሙትን ህገ-መንግስታዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ማፍረስ ሲሆን "የፍትህ ስርዓቱን ወደነበረበት መመለስ" በተከታይነት ይሰራል ብለዋል። ጄኔራሉ የታጠቁ ሃይሎች ከፌዴራል ሃይሎች ጋር መጠነኛ ግጭት በመፍጠር ሂደቱን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንም አብራርተው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግጭት እንዳያገረሽ በሚከላከል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት የፕሪቶሪያ ስምምነት የግዛትን ጨምሮ ሁሉም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለባቸው መደንገጉን አስታውሰዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ግን ትናንት  በማህበራዊ ትስስር…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ

የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ

አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው። የውድድሩ አዘጋጅ ቤይጂንግ ስፖርትስ ቢሮ ክስተቱን እየመረመርኩ ነው ሲል ለፈረንሳይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ቢቂላ እንዲሁም ኬንያውያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ማናንጋት ቻይናዊው አትሌት ሂ ጂ እንዲያሸንፍ ያደረጉበት ሁኔታን የተመለከቱ ቻይናውያን “ስፖርታዊ ሥነ ምግባር የሌለበት አሳፋሪ ተግባር” ሲሉ ገልጸውታል። ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተጋራው ቪዲዮ ላይ የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በእጃቸው ሲጠቁሙት ይታያሉ። በመጨረሻም…
ተጨማሪ ያንብቡ
በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው የራያ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ ወረዳ “የህወሓት ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት” ከቅዳሜ እስከ ዛሬ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ሲናገሩ፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን በበኩሉ ግጭት የተፈጠረው ታጣቂዎች በትግራይ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን ገልጿል። ከየካቲት ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገባቸው ካሉት የራያ ወረዳዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ የተከስ ልውውጡ በድጋሚ ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው እና የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ “የህወሓት ኃይሎች” በማለት የሚጠሯቸው ታጣቂዎች፤ ተኩስ የከፈቱት በወረዳው አዲስ…
ተጨማሪ ያንብቡ