በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ::

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱንአዲ ጊዜ  ከወጣው  የጨረታ ሰነድ ተመልክታለች።

የሊዝ ጨረታው በከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ላ የወጣ ጨረታ የለም፡፡

የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ም ተመልክተኛል፡፡

በኮሪደር ልማት በፈረሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም አካባቢ 22 ቦታዎች ለሊዝ ጨረታ ቀርበዋል። በዚህ አካባቢ ትልቁ ለሊዝ የቀረበው ቦታ 2,179 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ፣ ዝቅተኛ ስፋት ያለው መሬት ደግሞ 650 ካሬ ሜትር ነው።

በደረጃ አንድ ለተመደቡት ለ22ቱም ቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ በካሬ 2,213.25 ብር ተቆርጦላቸዋል። ለአንድ ካሬ ከፍተኛ መነሻ ዋጋ የተቆረጠላቸውም እነዚሁ በአራዳ ክፍለ ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም አቅራቢያ ላሉት ቦታዎች ነው።ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ከ150 በላይ ቦታዎችን በማቅረብ ቀዳሚው ነው።

የጨረታ ሰነዱ 2,300 ብር እየተሸጠ ሲሆን ፣ ጨረታው ከሚያዝያ 28 2016 አ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይከፈታል ተብሏል። የጨረታ አሸናፊዎች ቅድመ ክፍያ ያሸነፉበትን መሬት 40 በመቶ ሲሆን ቀሪው 60 በመቶ ክፍያ በአምስት አመታት ውስጥ ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ይጠበቃል። የሊዝ ዘመኑም ለ60 አመታት ነው።