የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ከመንግስት ጋር በማበር” ፓርቲውን ለማፍረስ ሞከሯል የሚል ክስ አቀረበ
ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በፓርቲው የቀድሞ አባላት ላይ ክስ መስርቻለሁ አለ፡፡ፓርቲው ክስ የመሰረተው “ቦርዱ የፓርቲው ውስጠ-ጉዳይ ላይ ጠልቃ በመግባት” እንዲሁም ከፓርቲው ከተሰናበቱት የቀድሞ አባላት ጋር በማበር የሀገሪቱን ህግና የኢፌዴሪ ህገመንግስት በተፃረረ መልኩ የተለያዩ “ህገወጥና አደገኛ ውሳኔ” በማስተላለፋቸው ነው ብሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለማፍረስ ከመንግስት ተልዕኮ ወስደው የፓርቲውን ህልውና ለአደጋ በማጋለጣቸው ምክንያት ከፓርቲው የተሰናበቱ አባላት ጋር ተባብሯል ሲል ከሷል። እንዲሁም ፓርቲው ከዚህ በፊት በዲሲፕሊን ጥሰት ምክንያት ከፓርቲው የተሰናበቱ ግለሰቦች የፓርቲውን ንብረትና መስሪያ ቤት አስረክበው በስርዓት መውጣት ሲገባቸው “ከመንግስት ተልዕኮ በመቀበልና በቦርዱ አጋዥነት ለቀው ባለመውጣታቸውና በፓርቲው ስም የተለያዩ ህገወጥ እንቅስቃሴ” እያደረጉ ይገኛሉ በተባሉት…
