የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ስብሰባ ጠራ
ጥር 08/2016 በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሊመክር እንደሆነ በአፍሪካ ህብረት እና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናት እና ምርምር የሚያደርገው “አማኒ አፍሪካ” አስነብቧል፡፡በስብሰባው ላይ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማብራሪያ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ ስብሰባውን በንግግር የሚከፍቱት የዚህ ወር የምክር ቤቱ ሊቀመንበር የሆኑት፤ በአፍሪካ ህብረት የጋና አምባሳደር አማ ቱም-አሙሃ ናቸው። እርሳቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴዎዬ፤ ጉዳዩን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ገለጻ እንደሚሰጡ “አማኒ አፍሪካ” አስታውቋል። በአፍሪካ ግጭቶችን የመከላከል እና ከተከሰቱም በኋላ የመቆጣጠርና መፍትሄ የማበጀት ዓላማ ያለው የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት 15 አባል…
