<<መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።>> ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 60 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሁለተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችንና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል። ኢሰመኮ በአፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ክልሎች በግጭት እና ሌሎች ሰው ሠራሽ መንሥዔዎች የተፈናቀሉ ከ369 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ ተመላሾችን…
