በዳግም ሲሳይ ተጽፎና ዳይሬክት የተደረገው “የፋሲካ ሌሊት” አዲስ ፊልም በቅርቡ ለተመልካች ይቀርባል ተብሏል።
ፊልሙ በሁለት የማይገናኙ ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ ጥንዶች ባልታሰበ አጋጣሚ በፋሲካ ዋዜማ ሌሊት ተገናኝተው የሚያሳልፉትን የተለያዩ ክስተቶች የሚቃኝ ጭብጥ አለው፡፡
መስከረም አበራና ቸርነት ፍቃዱ ሙሉ ፊልሙ ላይ የሚታዩበት ሲሆን አስደናቂ ትወናቸውንም አሳይተውበታል፡፡
ቀረፃው በአዲስ አበባ አውራጎዳናዎች መንገድ በማዘጋትና በተለያዩ ቦታዎች የተሰራ ነው፡፡
በጀርመን ሀገር በተካሄደው European Work in Progress ላይ በመሳተፍ፤ ከ250 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ አለማቀፍ የፊልም ፈስቲቫል ተወካዮችና ፊልም አሰራጭ ድርጅቶች በተገኙበት ለእይታ ቀርቧል ተብሏል፡፡
ፊልሙ የአለማቀፍ ፌስቲቫሎች የጊዜ ሰሌዳ ካልተቀየር በስተቀር በተያዝው አመት መጋቢት ወር ላይ በሀገር ውስጥ ሲኒማ ቤቶች ላይ የሚለቀቅ ይሆናል ሲል ሄስትሪ ፊልምስ አስታውቋል፡፡
ከታሪኩ መነሻ አንስቶ እስከ ቅንብር መጨረሻ ድረስ ፊልሙ በሄስትሪ ፊልምስ የተመረተ ሲሆን የፊልሙ መጨረሻ ማስተሪንግ በጀርመን ሀገር እንደሚሰራ ተገልጿል።
