22 ጋዜጠኞች መሞታቸው ተነገረ

cpj

ጥቅምት 10/2016  

ሲፒጄ የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ከጀመረ አንስቶ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች ተገድለዋል አለ።

የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ (ሲፒጄ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገደሉት ጋዜጠኞች መካከል 18ቱ ፍልስጤማውያን ናቸው ብሏል።

የሲፒጄ መግለጫ እንደሚያብራራው 15 ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡት በእስራኤል የአየር ጥቃት ሲሆን ሁለት ጋዜጠኞች ደግሞ በደቡባዊ እስራኤል በሐማስ ጥቃት የተገደሉ ናቸው።

ቡድኑ በመግለጫው 8 ጋዜጠኞች ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጸ ሲሆን ሦስት ጋዜጠኞች የደረሱበት እንደማይታወቅ ምናልባትም በእስር ላይ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።

ሲፒጄ ጋዜጠኝነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በመግለጽ ታጣቂዎች ሞያውንና ባለሞያዎቹን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡