ካቻ “የግልየክፍያሰነድአዉጪ” በመሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ

kacha

ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2016

በኢትዮጵያ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት ላይ የተሰማራው ካቻ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት አክሲዮን ማሕበር፤ በአገሪቱ የመጀመሪያው “የግል የክፍያ ሰነድ አዉጪ” በመሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ መጀመሩን ትናንት ሐሙስ ምሽት ጥቅምት 8/2016 በስካይላይት ሆቴል በነበረው መርሃ ግብር ላይ አብስሯል።

በዚህም መሰረት የሞባይል የገንዘብ ዝውውር አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ሰነዶችን ለማውጣት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ የመጀመርያው የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ መሆን ችሏል።

ካቻ ከአለም አቀፍ ሐዋላ አስተላላፊዎች ጋር በፈጠረው አጋርነት ደህንነቱ የተጠበቀ የውጪ ሐዋላን በማሳለጥ፤ ላኪዎችም ሆኑ ተቀባዮች ተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎቶች ዕድል የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጿል።

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአሰራር ስርዓት ዓለም አቀፍ የሐዋላ አስተላላፊዎች ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመናበብ እና ገንዘብ ለማስገባት የሚወስድባቸውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት፤ ከካቻ ጋር በሚፈጥሩት የሥራ አጋርነት ወደ ኹሉም የባንክ እና የሞባይል ገንዘብ ሂሳቦች ገንዘብ ማስተላለፍ የሚችሉበት ስርዓት ነው።

የዚህ አገልገሎት ወደ ሥራ መግባት የካቻ አጋር ባንኮች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኙ በር የሚከፍት መሆኑ ተነግሯል።

ካቻ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የዲጂታል ብድሮች፣ ያለ ካርድ በኢቲኤም ማሽኖች እንዲሁም በወኪል አማካኝነት ገንዘብ የማውጣት፣ የአየር ሰዓት መሙላት እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ ኹለንተናዊ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።