እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ትናንት ሌሊት በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 55 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን ሐማስ አስታወቀ።
በዚህ የአየር ጥቃት 30 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውንም ኤኤፍፒ ሐማስን ዋቢ አድርጓል።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምትፈጽመውን የአየር ጥቃት አጠናክራ እንደምትቀጥል እና የእግረኛ ጦሯንም ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።
በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያንም ሙሉ በሙሉ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱም ጦሩ እያስጠነቀቀ ይገኛል።
የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ጥቃቱ በጋዛ ድንበር አካባቢ ለተከማቸው የእስራኤል ጦር ላይ የደቀነውን አደጋም ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል።
ከጋዛ በተጨማሪ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።
ጦሩ የ”አሸባሪዎች ማዘዣ ማዕከል” እንደሆነ የገለጸውን በጄኒን የስደተኞች መጠለያ የሚገኘው መስጂድን ኢላማ አድርጌያለሁ ብሏል።
የዜናው ምንጭ ቢቢሲ ነው።
