በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱ ተገለጸ
ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2016 በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል። በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የምታቀርበውን ስድስት አዲስ የቃል ኪዳን ሰነድ ለማጽደቅ የተዘጋጀ የከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከተለያዩ አገራት የመጡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። እኤአ በ2019 በተካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች…
