አርብ ጥቅምት 15 /2016
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ “ሐሰተኛ” ሪፖርት አውጥቷል በማለት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ምላሽ ከሷል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉበት ወቅት ኮሚሽኑ ይህን ሪፖርት ማውጣቱ፣ “ኃላፊነት የጎደለው” እና “ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ኾን ተብሎ የተሠራ” ነው በማለት ወቅሷል።
የክልሉ አስተዳደር አያይዞም፣ ፌደራል መንግሥቱ ወደፊት ተመሳሳይ ሪፖርቶች እንዳይወጡ፣ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
