ጥቅምት 15/2016
ሄመን በቀለ የተባለ ትውልደ ኢትዮጲያዊ የቆዳ ካንሰርን መከላከል ይችላል የተባለውን ሳሙና ለውድድር ይዞ በመቅረብ 25 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማሸነፍ መቻሉ ታውቋል፡፡ በዚህም የአሜሪካ ወጣት ምርጥ ተመራማሪ ክብርን ማግኘት ችሏል፡፡
ታዳጊው ሳሊሳይከሊክ አሲድ፤ ግላይኮሊክ እና ትሪቲንይን የተባሉ የቆዳን በሽታን የመከላከል አቅምን የሚያሳድጉ ውህዶችን በመጠቀም ሳሙናውን እንደሰራውም ተናገሯል፡፡
የቆዳ ካንሰር በአብዛኛው በታዳጊ ሀገራት በሚገኙ ዜጎች ላይ ይከሰታል፡፡ በቀላሉ መከላከል የምንችላቸው በሽታዎች በቆይታ ከፍተኛ ወጪ ያስወጡናል የሚለው ታዳጊው በ0.05 ዶላር ለገበያ የሚውሉ ሳሙናዎችን በመሰራት ለገበያ አቅርቧል፡፡
ታዳጊው የተሸለመውን 25 ሺህ ዶላር የፈጠራ ስራውን በስሙ ለማስመዝገብ እና በኮሌጅ በሚኖረው ቆይታ ምርምሩን አጠናከሮ ለመቀጠል እንደሚያውለው ተናግሯል፡፡
በመጨረሻም ታዳጊው በ2028 የሳሙናውን ምርቶች ለታዳጊ ሀገራት በነፃ የሚያከፋፍል ግብረ ሰናይ ድርጅት ለማቋቋም ማቀዱን ኢን ቢ ሲ ኒውስ ዘግቧል፡፡
