በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአለም አቀፍ ፍ/ቤቶች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016

በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን አገራትና ተቋማት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤቶች ጭምር ተጠያቂ እንዲኾኑ ጥረት እንዲያደርጉ ረቡዕ’ለት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት ጠይቋል።

ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ኹኔታ መከታተሉንና ለጦርነቱ ተጎጂዎች ድጋፍ መስጠቱን እንዳያቋርጥም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ፣ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቀጠሉበት ወቅት ቆይታ ጊዜው እንዲያበቃ መደረጉ ስህተት መኾኑንም ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ገልጧል።