አዲስ ጊዜ

230 Posts

በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአለም አቀፍ ፍ/ቤቶች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን አገራትና ተቋማት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤቶች ጭምር ተጠያቂ እንዲኾኑ ጥረት እንዲያደርጉ ረቡዕ'ለት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት ጠይቋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ኹኔታ መከታተሉንና ለጦርነቱ ተጎጂዎች ድጋፍ መስጠቱን እንዳያቋርጥም ኮሚሽኑ አሳስቧል። ኮሚሽኑ፣ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቀጠሉበት ወቅት ቆይታ ጊዜው እንዲያበቃ መደረጉ ስህተት መኾኑንም ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ገልጧል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ "ሐሰተኛ" ሪፖርት አውጥቷል በማለት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ምላሽ ከሷል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉበት ወቅት ኮሚሽኑ ይህን ሪፖርት ማውጣቱ፣ "ኃላፊነት የጎደለው" እና "ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ኾን ተብሎ የተሠራ" ነው በማለት ወቅሷል።የክልሉ አስተዳደር አያይዞም፣ ፌደራል መንግሥቱ ወደፊት ተመሳሳይ ሪፖርቶች እንዳይወጡ፣ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

ጥቅምት 12 ፤2016 ፤አዲስ አበባ )  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸ በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፤ምክር ቤታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸውና በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱት ሪፖርቶች ተገንዝቧል፡፡በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 4 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ‹ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ሃሳቦች፤አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱ ተገለጸ

ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2016 በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል። በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የምታቀርበውን ስድስት አዲስ የቃል ኪዳን ሰነድ ለማጽደቅ የተዘጋጀ የከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከተለያዩ አገራት የመጡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። እኤአ በ2019 በተካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች…
ተጨማሪ ያንብቡ
የ14 አመቱ ትውልደ ኢትዮጲያዊ ታዳጊ የቆዳ ካንሰርን መከላከል የሚችል ሳሙና ሰራ፡፡

የ14 አመቱ ትውልደ ኢትዮጲያዊ ታዳጊ የቆዳ ካንሰርን መከላከል የሚችል ሳሙና ሰራ፡፡

ጥቅምት 15/2016 ሄመን በቀለ የተባለ ትውልደ ኢትዮጲያዊ የቆዳ ካንሰርን መከላከል ይችላል የተባለውን ሳሙና ለውድድር ይዞ በመቅረብ 25 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማሸነፍ መቻሉ ታውቋል፡፡ በዚህም የአሜሪካ ወጣት ምርጥ ተመራማሪ ክብርን ማግኘት ችሏል፡፡ታዳጊው ሳሊሳይከሊክ አሲድ፤ ግላይኮሊክ እና ትሪቲንይን የተባሉ የቆዳን በሽታን የመከላከል አቅምን የሚያሳድጉ ውህዶችን በመጠቀም ሳሙናውን እንደሰራውም ተናገሯል፡፡የቆዳ ካንሰር በአብዛኛው በታዳጊ ሀገራት በሚገኙ ዜጎች ላይ ይከሰታል፡፡ በቀላሉ መከላከል የምንችላቸው በሽታዎች በቆይታ ከፍተኛ ወጪ ያስወጡናል የሚለው ታዳጊው በ0.05 ዶላር ለገበያ የሚውሉ ሳሙናዎችን በመሰራት ለገበያ አቅርቧል፡፡ታዳጊው የተሸለመውን 25 ሺህ ዶላር የፈጠራ ስራውን በስሙ ለማስመዝገብ እና በኮሌጅ በሚኖረው ቆይታ ምርምሩን አጠናከሮ ለመቀጠል እንደሚያውለው ተናግሯል፡፡በመጨረሻም ታዳጊው በ2028 የሳሙናውን ምርቶች ለታዳጊ ሀገራት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው::

አሜሪካ ጆርጂያ ግዛት የሚገኘው ትሪኒቲ ኢንተርናሽናል አምባሳደርስ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት እንዳበረከተላቸው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታወቁ። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ለሌሎች ሃገራት መሪዎች አርአያ የሚሆን ስራ በመስራታቸው የጆርጂያ ግዛት የክብር ዜግነት ሽልማት እንደተበረከተላቸው የግዛቱ ሴናተር ጋይል ዴቨንፓርት በመድረኩ ላይ ተናግረዋል ተብሏል:: ከንቲባዋ ለተሰጠኝ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እና የጆርጂያ ግዛት ላበረከተልኝ የክብር ዜግነት አዋርድ እንዲሁም የአትላንታ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ ላደረጉልኝ አቀባበል ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ ብለዋል። በተጨማሪም ከከንቲባ አንድሬ ዲከንስ ጋር በነበረን ቆይታ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጎንደር ዲስትሪክቱን ወደ ሽሬ ለማድረግ የጀመረው እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጠመው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጎንደር ዲስትሪክቱን ወደ ሽሬ ለማድረግ የጀመረው እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጠመው

ጥቅምት 12/2016 የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎንደር ዲስትሪክት የነበረውን ወደ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ለማዞር የጀመረው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጿል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ውስጥ ሲሰጠው የነበረው አገልግሎት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ተቋርጦ ቆይቶ ነበር ብለዋል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ዲስትሪክቱን ጎንደር በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሆኖም፣ በአሁኑ ሰዓት በተቋሙ የተዘረጋው ሥርዓት ስራ ሊያጓትት የሚችልና በህዝብ ዘንድ ቅሬታን የሚያስነሳ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ወቅሰዋል፡፡ በአራቱም የአገልግሎት ማእከላት ማለትም ዳንሻ፣ ባህከር፣ አድረመጥ እና ሁመራ የሚገኙ የባለሙያዎችን ደሞዝ ጭምር ወደ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው ተነገረበዳግም ጌታቸው

ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው ተነገረበዳግም ጌታቸው

ጥቅምት 12/2016 በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን ለአዲስ ጊዜ ገለፁ፡፡አክሱም ከተማ በቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተች ከተማ መሆኗን የገለፁት ሀላፊው በጦርነቱ ከወደሙት ቅርሶች ባለፈ የተዘረፉና የጠፉ 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊው ጨምረው፣ የነዚህ ቅርሶች መጥፋት በከተማዋ የቱሪዝም እንቀስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አብራርተዋል፡፡የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ሀላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን እንደገለጹልን፣ ጽሕፈት ቤታቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
ዳግም የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፀጥታ ችግር እንቅፋት እንደሆነ

ዳግም የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፀጥታ ችግር እንቅፋት እንደሆነ

ጥቅምት 12/2016በጣና ሀይቅና በዙሪያው በድጋሚ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው የጣና ሀይቅ እና ሌሎች ውሀማ አካላት ኤጀንሲ ገልጿል።ሀሳባቸውን ለአዲስ ጊዜ የሰጡት የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ መልካሙ አዳም በበኩላቸው አረሙ መስፉፉቱን መመልከታቸዉን አንስተው ከዚህ ቀደም ችግሩን ለመከላከል ኮሚቴ መዋቀሩን ተናግረዋል።የጣና ሀይቅ እና ሌሎች ዉሀማ አካላት ኤጀንሲ ሀላፊው አቶ ፈንቴ አለም የእምቦጭ አረሙ ምን ያህል ሄክታር እንደተስፋፋ መረጃዉ እንደሌላቸው አንስተው ባለው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ችግሩን ለመቅረፍ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጋቸውን ገልፀዋል።ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የባሕር ዳር ነዋሪዎች እንደነገሩን እየተስፋፋ የመጣው አረም በአፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው የሀይቁ ቱሪዝም ላይ እክል እንዳይሆን ስጋት እንዳደረባቸው አንስተዋል።እንደከዚህ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ተነገረ

በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ተነገረ

ሰኞ ጥቅምት 12/2016   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ አዲስ ባወጣው የሩብ ዓመት ሁኔታዊ ሪፖርት በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ያህል ትምህርት ቤቶች በሙሉ እና በከፊል ዝግ መሆናቸውን ገልጿል። በዚህም 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጨ መሆናቸውን አስታውቋል። የትምህርት ቤቶቹ መዘጋትም ሆነ የህጻናቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆን በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ችግር መሆኑን የጠቆመው የዩኒሴፍ ሪፖርት በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት ለችግሩ መስፋፋት በቀዳሚነት የተቀመጠ ምክንያት ሆኗል። በዩኒሴፍ የተቀመጠው በሙሉ እና በከፊል የተዘጉ ትምህርት ቤቶች አሀዝ ሀያ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ቁጥር እንደሚሸፍን ሪፖርቱ በማብራሪያው ላይ አስቀምጧል። ድርጅቱ በማጠቃለያው ላይ ጊዜው…
ተጨማሪ ያንብቡ