የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ::
የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ “የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል” ብሏል። ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው “ጽንፈኛ” ባላቸው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል። የኢትዮጵያ ባህር ሀይል የባህር ሃይል ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እንደተሰማሩ እና ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም አዛዡ መናገራቸው ተገልጿል። የባህር ሃይል ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል እንደሆነም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ ተናግረዋል ተብሏል። የባህር ሃይል ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ…
