የአሜሪካው የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡
09/05/2016 የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ካምፓላ እና አዲስ አበባ ይጓዛሉ ብሏል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በመግለጫው ። አምባሳደር ሐመር በካምፓላ ፤ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ላይ በሚያተኩረው 42ኛው የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል። አምባሳደር ሐመር ከካምፓላ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ ገልጿል።በኡጋንዳ መዲና ዛሬ የሚካሄደው የኢጋድ ስብሰባ ከያዛቸው ሁለት መወያያ ርዕሶች አንደኛው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው።ኢጋድ ይህን በተመለከተ ውይይት ለማድረግ ስብሰባ መጥራቱን ያወደሰችው አሜሪካ ተወካይዋ አምባሳደር ሐመር…
