ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ‹‹ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥም ቢሆን በጋዜጠኞችና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት ህጋዊ ስርአትን የተከተለ ሊሆን ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት
ጥቅምት 12 ፤2016 ፤አዲስ አበባ ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸ በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው፤ምክር ቤታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የህትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈፀመባቸውና በዚህም ሳቢያ ተቋማቱ የእለት ተዕለት ስራዎቻቸውን ለመስራት መቸገራቸውን ከደረሱት ሪፖርቶች ተገንዝቧል፡፡በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 29 ንዑስ አንቀፅ 4 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው ‹ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፤ሃሳቦች፤አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ…
