አዲስ ጊዜ

230 Posts
“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርት በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቀሰ።

“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርት በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቀሰ።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ከቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት መገምገሙን በተመለከተ  በሰጡት መግለጫ መንግስት ዜጎች ወደ መበደበኛ ኑሯቸው እንዲመለሱና መሰረታዊ መብቶቻቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቁ በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር ተግባራትን ሰርቷል ብለዋል፡፡መንግስት በኢትዮጵያ ነጻና ገለልተኛ ተቋማት እንዲገነቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑንንና ለዚህም ማሳያ አንዱ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አንዱ መሆኑ የተናገሩት ሚኒስትሩ ነጻና ገለልተኛ መሆን ግን ከአስፈጻሚ አካላት ብቻ ሳይሆን ከባዕዳንና ከሌሎች የውስጥ ሰርጎ ገቦች ሊሆን ይገባል ሲሉ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ሚኒስትሩ…
ተጨማሪ ያንብቡ
“በደራ 3 አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል ከ10 በላይ ካህናት ተገለዋል” ማኅበረቅዱሳን

“በደራ 3 አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል ከ10 በላይ ካህናት ተገለዋል” ማኅበረቅዱሳን

በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት  3 አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው እና  ከ10 በላይ አገልጋይ ካህናት መገደላቸው ተገልጿል።ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት ከ400 በላይ  መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ተገልጿል።ከደረሰው ጥቃት በኃላ  ከ8 ወረዳዎች  በርካታ ዜጎች  ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደዋል፡፡ችግሩን ለመፍታት የሚመለከተው አካል ምንም አይነት ጥረት እያደረገ ባለመሆኑ የምእመናኑ የመኖር ህልውና በአደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ለከባድ እንግልትም መዳረጋቸው ማኅበረ ቅዱሳን አስታውቋል።በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ ታጠቁ ኃይሎች  በእምነቱ ተከታዮች ላይ ባነጣጠረ መልኩ በተፈጸመው ጥቃት በተለይም በገጠሩ ክፍል የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተክርስቲያናት መዘጋጀታቸውን እና በደረሰው ጉዳት ቤተክርስቲያን አገልግሎት መስጠት መቆሙን  ማኅበረ ቅዱሳን ገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ
ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭቱን ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ተነገረ።

ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭቱን ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ተነገረ።

ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2016 በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት ከፊታችን አርብ ጥቅምት 23/2016 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡ በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ መስፍን አሰፋ፤ የሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት የፊታችን አርብ ዳግም እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የአንድ ዳቦ ዋጋ 5፡00 ብር መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው፤ በአቅርቦት ረገድም በኹሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚያመርተው ድርጅቱ በተለይ ከስንዴ አቅርቦትና ግዢ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ክፍተት ምርቱ በመዲናዋ ማሰራጨት ካቆመ ከስድስት ወራት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለመዲናዋ ከ465 ሺህ በላይ ሰራዊት መቋቁሙን ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለመዲናዋ ከ465 ሺህ በላይ ሰራዊት መቋቁሙን ይፋ አደረገ።

ረዕቡ ጥቅምት 21/2016 ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የበጀት አመቱን ሩብ አመት የስራ እቅድ አፈፃፀም ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ሰራዊቱ ምንም አይነት ፋይናንስ ድጋፍ እንደማይደረግለት እና በነጻ የሚሰራ ሰራዊት መሆኑን በከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዋ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ኃብት ጉባዔ በመጭው ሕዳር ወር በኢትዮጵያ ይካሄዳል

የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ኃብት ጉባዔ በመጭው ሕዳር ወር በኢትዮጵያ ይካሄዳል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የሚያሰናዳው የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ጉባዔ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተነገረ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጭው ሕዳር ወር የሚከናወነው የአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ጉባዔ በአካል እና በድረ ገጽ በቅይጥ መልኩ እንደሚሰናዳ የገለጸ ሲሆን፤ አካላዊው መድረክ ደግሞ አዲስ አበባ በሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት አዳራሽ እንደሚካሄድ አስታውቋል። የአህጉሪቱ ትልቁ የምርምር እና የምጣኔ ሃብት መሰባሰቢያ የሆነው ይህ መድረክ የአህጉሪቱን ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተባባሪዎች እና ቁልፍ የሆኑ የመንግሥት እና የግልም ኩባንያዎች ወኪሎች እንዲሁም እውቅና ጀማሪ ተመራማሪዎችን ያሳትፉበታል ተብሏል። ጉባዔው መከናወን የጀመረው በግሪጎሪያን አቆጣጠር በ2006 ሲሆን፤ በዚህ ዓመት በዘላቂ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተነግሯል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ፡፡

 በ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡- 1. 1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል። 2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ 3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሰላም እጦት ግብር የመሰብሰቡን ስራ አዳጋች አድርጎታል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ

የሰላም እጦት ግብር የመሰብሰቡን ስራ አዳጋች አድርጎታል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ

ጥቅምት 20/2016  የአማራ ክልላዊ መንግስት በዘንድሮ በጀት ዓመት 71 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በሩብ ዓመቱ መሰብሰብ የቻለው 6 ቢሊዮን 264 ሚሊየን ብቻ መሆኑን አስታወቀ። አብዛኛዎቹ የክልሉ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚጠበቅባቸውን ገቢ በመሰብሰብ ረገድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ገቢ ከሌለ የህክምና ተቋማት እና ት/ቤቶች ይዘጋሉ፤ የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ይቆማል፤ ልማት፣ እድገት፣ ብልጽግና አይኖርም ሲሉ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ደጀኔ መናገራቸውን መረጃው አካቷል። በ2016 በጀት ዓመት 71 ነጥብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጎጎትበፓርቲው አመራር አቶመላኩሳህሌላይየተፈፀመውን እገታበማውገዝ መግለጫ አወጣ፡፡

ጎጎትበፓርቲው አመራር አቶመላኩሳህሌላይየተፈፀመውን እገታበማውገዝ መግለጫ አወጣ፡፡

የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መላኩ ሳህሌ በቀን 14/02/2016 ዓ.ም ከቤታቸው አቅራቢያ ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል ያለው ፓርቲው ጥቅምት 16 አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት አቶ መላኩ ሳህሌ ፖሊስ "ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር እና ከጠላት ጋር በማበር" የሚል  ክስ ቢያቀርብባቸውም ችሎቱ በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ብሏል። በዚሁ መሰረት የዋስትና ብር ተከፍሎ አቶ መላኩ ከፖሊስ ጣቢያ ይወጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፖሊስ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አዛውሮአቸው እስካሁኑ ሰአት ድረስ በእገታ ላይ ይገኛሉ ያለው መግለጫው ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ የተፈቀደላቸውን…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአየር ንብረት ለውጥ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ

የአየር ንብረት ለውጥ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ

በዘላቂ የልማት ግቦች እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚያጠነጥን የግማሽ ቀን አውደ-ጥናት ትናንት ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱን አዲስ ጊዜ አይታለች፡፡ ኤንዳ ኢትዮጵያ በመባል በሚታወቀው እና በዋናነት በከተማ ልማት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በሚሰራው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ መርሀ-ግብር ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን በተለያዩ የዜና ማሰራጫ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሐን ባለሞያዎችም የውይይቱ አካል ነበሩ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ምልክቶች እና እያስከተሉ ያሉት መጠነ ሰፊ ጉዳቶች በአውደ-ጥናቱ ላይ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ በተለይ፣ ችግሩ ከኢትዮጵያ አንጻር የተዳሰሰበት ክፍል በተሳታፊዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንደነበር መታዘብ ተችሏል፡፡ እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ይሳካሉ ተብለው ግብ የተያዘላቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ መንግስት ሰላም ለማምጣት መስራት አለበት ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ መንግስት ሰላም ለማምጣት መስራት አለበት ተባለ፡፡

የሰሜን ኢትዮጵያዉን ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ ከተጣሉት ማዕቀቦች ዉስጥ አንዱ የአጎዋ ነጻ የንግድ እድልን ማጣት ነው፡፡ እገዳው አሁንም አልተነሳም፡፡የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጎሹ ነጋሽ  እንደተናገሩት ፤ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፉ በእቀባዉ መጎዳቱን ተናግረዉ ኢትዮጵያ የአጎዋ እድልን ዳግመኛ እንድታገኝ ሰላም በማምጣት በኩል የቤት ስራዋን መስራት አለባት ብለዋል።እግዱ ከተላለፈ በኋላ የታጣዉን የንግድ እድል ለማካካስ የተለያዩ ስራዎች በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መሰራታቸዉን ያነሱት አቶ ጎሹ ፤ የገበያ ትስስርን መፍጠር ዋነኛዉ መሆኑን ጠቁመዋል።ሀላፊው ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ባሉ የጨርቃጨርቅ አምራቾች የንግድ ትስስር ይፈጥራል የተብሎ የታመነበት አፍሪካ ሶርሲንግ እና የፋሽን ሳምንት ለ10ኛ ጊዜ በአዲስአበባ ስካይላይት ሆቴል ከጥቅምት 23- 26  እንደሚካሄድ…
ተጨማሪ ያንብቡ