“በደራ 3 አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል ከ10 በላይ ካህናት ተገለዋል” ማኅበረቅዱሳን


በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት  3 አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው እና  ከ10 በላይ አገልጋይ ካህናት መገደላቸው ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ ባደረሱት ጥቃት ከ400 በላይ  መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ተገልጿል።

ከደረሰው ጥቃት በኃላ  ከ8 ወረዳዎች  በርካታ ዜጎች  ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የሚመለከተው አካል ምንም አይነት ጥረት እያደረገ ባለመሆኑ የምእመናኑ የመኖር ህልውና በአደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ለከባድ እንግልትም መዳረጋቸው ማኅበረ ቅዱሳን አስታውቋል።

በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ደራ ወረዳ ታጠቁ ኃይሎች  በእምነቱ ተከታዮች ላይ ባነጣጠረ መልኩ በተፈጸመው ጥቃት በተለይም በገጠሩ ክፍል የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተክርስቲያናት መዘጋጀታቸውን እና በደረሰው ጉዳት ቤተክርስቲያን አገልግሎት መስጠት መቆሙን  ማኅበረ ቅዱሳን ገልጿል።