ጎጎትበፓርቲው አመራር አቶመላኩሳህሌላይየተፈፀመውን እገታበማውገዝ መግለጫ አወጣ፡፡

የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መላኩ ሳህሌ በቀን 14/02/2016 ዓ.ም ከቤታቸው አቅራቢያ ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል ያለው ፓርቲው ጥቅምት 16 አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት አቶ መላኩ ሳህሌ ፖሊስ “ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር እና ከጠላት ጋር በማበር” የሚል  ክስ ቢያቀርብባቸውም ችሎቱ በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ብሏል።

በዚሁ መሰረት የዋስትና ብር ተከፍሎ አቶ መላኩ ከፖሊስ ጣቢያ ይወጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፖሊስ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አዛውሮአቸው እስካሁኑ ሰአት ድረስ በእገታ ላይ ይገኛሉ ያለው መግለጫው ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ የተፈቀደላቸውን ግለሰብ ፖሊስ ሊለቃቸው አልፈቀደም ይሄም የእስሩን ፖለቲካዊነት ግልፅ የሚያደርግ ነው ብሏል።

ፓርቲያችን የአመራሩን ሁኔታ በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተለው እና የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ይገኛል ያለው መግለጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የፍትህ፣ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጉዳይ የሚገዳቸው  ሐገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ተቋማት፣ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ጉዳዩን በጥብቅ እንዲከታተሉት፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር ግፊት በማድረግ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡