የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ከቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት መገምገሙን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ መንግስት ዜጎች ወደ መበደበኛ ኑሯቸው እንዲመለሱና መሰረታዊ መብቶቻቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቁ በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር ተግባራትን ሰርቷል ብለዋል፡፡
መንግስት በኢትዮጵያ ነጻና ገለልተኛ ተቋማት እንዲገነቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑንንና ለዚህም ማሳያ አንዱ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አንዱ መሆኑ የተናገሩት ሚኒስትሩ ነጻና ገለልተኛ መሆን ግን ከአስፈጻሚ አካላት ብቻ ሳይሆን ከባዕዳንና ከሌሎች የውስጥ ሰርጎ ገቦች ሊሆን ይገባል ሲሉ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ሚኒስትሩ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በመግለጫው ላይ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ጠቅሰው እነዚህ ተቋማት የሚያቀርቡት ሪፖርት ሁሉ ነጻና ገለልተኛ ነው ብሎ መውሰድ እንደማይገባም ተናግረዋል፡፡
“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርት በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቀሰ።
