ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2016
በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት ከፊታችን አርብ ጥቅምት 23/2016 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ መስፍን አሰፋ፤ የሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት የፊታችን አርብ ዳግም እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት የአንድ ዳቦ ዋጋ 5፡00 ብር መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው፤ በአቅርቦት ረገድም በኹሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚያመርተው ድርጅቱ በተለይ ከስንዴ አቅርቦትና ግዢ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ክፍተት ምርቱ በመዲናዋ ማሰራጨት ካቆመ ከስድስት ወራት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።
