አዲስ ጊዜ

227 Posts
ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን ከኢጋድ አባልነቷ ለቀቀች

ሱዳን፣ ኢጋድ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብቷል በማለት ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ዛሬ አስታውቃለች። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነችው ጅቡቲ አቻቸው በጻፉት ደብዳቤ፣ ይህንኑ ውሳኔ አሳውቀዋል። ሱዳን ከኢጋድ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ በመጭው ሐሙስ ኡጋንዳ ላይ የተጠራው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባዔ ወታደራዊውን መንግሥት ሳያማክር የሱዳኑን ጦርነት አጀንዳው ማድረጉንና የፈጥኖ ደራሹን ኃይል እንዲገኙ መጋበዛቸውን በመቃወም ነው። የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በኢጋድ ጉባኤ ላይ እንደማይገኙ ከትናንት ወዲያ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢጋድ አስቸኳዩን የመሪዎች ጉባኤ የጠራው፣ በሱዳኑ ጦርነት ዙሪያ ለመወያየትና የኢትዮጵያና ሱማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን ለማብረድ ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ
ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎቶች ለማግኘት ዲጅታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሊሆን ነው

ኢትዮጵያዊያን የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት የዲጂታል መታወቂያን ግዴታ ወደ መሆን ሊሸጋገር እንደደሆነ  የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ዳይሬክተር ዮዳሔ ዘሚካኤል ተናግረዋል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በኩል በተለያዩ ምዕራፎች ይተገበራል ከተባለው የምዘገባ ሂደት በኋላ  ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት እንደሚታገዱ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡  ዳይሬክተሩ፣ ተቋማት ዲጂታል መታወቂያ ያልያዙ ደንበኞቻቸውን አገልግሎት የመንፈግ ሕጋዊ መብት አላቸው ማለታቸውም ተገልጧል። እስከ አሁን አገልግሎቱን ለማግኘት አራት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 መታወቂያ ለማግኘት ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸውን ሁሉንም ዜጎች ለመመዝገብ ተይዞ የነበረው ቀነ-ገደብ ወደ 2028  ተሸጋግሯል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

በእናቶችና አረጋውያን ሴቶች ላይ ግርዛት እየተፈጸመ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን በሻሸጎ ፣ ሶሮና ምዕራብ ሶሮ ወረዳዎች በሴቶች ላይ በሚፈጸም ግርዛት ዙሪያ ባከናወነው ክትትል የተለዩ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል። በሻሸጎ ወረዳ በማኅበረሰቡ ዘንድ ‘ጨበላ’ በመባል የሚታወቅ የተደጋጋሚ ግርዛት ጎጂ ልማድ በአካባቢው በበጋ ወራት በሁሉም ዕድሜ ክልል በሚገኙ ሴቶች ላይ በስፋት እንደሚፈጸም እንዲሁም ሴቶችና ሴት ሕፃናት መራቢያ አካላቸው አካባቢ ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እንደመፍትሔ የሚወሰድ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ጎጂ ልማድ የሚያልፉ ሴቶች ከጤና እክል ጀምሮ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት የሚደርስባቸው መሆኑ በክትትሉ ከተለዩ ግኝቶቹ መካከል መሆኑን ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ተጎጂዎች ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እየተሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አጥጋቢ አለመሆን ሴቶች…
ተጨማሪ ያንብቡ
አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

አሜሪካ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማፅዳት የምታደርገውን ዘመቻ እደግፋለሁ አለች::

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የአሜሪካ መከላከያ ኃይልና የኢምባሲው የጸጥታ ትብብር ቢሮ ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፈንጂዎችንና ያልፈነዱ የመድፍ ጥይቶችን ለማጽዳት እያደረገች ያለውን ዘመቻ ለማገዝ ከኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ተቋም ጋር የጋራ ፕሮጀክት መጀመራቸውን  አስታውቋል። ኢምባሲው፣ ኢትዮጵያ ፈንጂዎችን ለማጽዳት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ፣ ፔንታጎን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በትብብር የሚሠሩ ባለሙያዎችን መላኩን ገልጧል።የቡድኑ አባላት ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰብዓዊ ፈንጂ ማምከን ማሰልጠኛ ማዕከል እና ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጦር መሳሪያ ማስወገድ እና ቅነሳ ፕሮግራም የተውጣጡ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ  ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የዳሰሳ ጥናቱን እና ቀጣይ ድጋፎችን በተመለከተም  የኤምባሲው ተወካዮች እና የባለሙያዎች ቡድኑ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊዎች ጋር   ጥር 6፤ 2016…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም!

መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም!

እናት ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም ሲል አሳሰበ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቤተክርስቲያን ክብረ በዓላት የቤተክርስቲያኒቷን ዶግማ፣ ቀኖናና ሥርዓት ጠብቀው እንዳይከወኑ የሚያደርጉ መንግሥታዊ ጫናዎች ተበራክተዋል ያለው ፓርቲው እንዲህ ያለው ተጽዕኖ ካረፈባቸው በዓላት ውስጥ የጥምቀት ክብረ በዓል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው ብሏል። ይህንኑም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት "የጥምቀት በዓል አከባበርን እና ወቅታዊ ጉዳዮችን" መሠረት አድርጎ ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ከተሰጠው መግለጫ ፓርቲያችን ለመረዳት ችሏል ብሏል በመግለጫው። በዓሉ የአለም ቅርስ እንደመሆኑ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በክብረ በዓሉ የሚሳተፉ ምዕመናንና ጎብኚዎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ ለበዓሉ ስኬታማነት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የከተሞች የልምድ ልውውጥ አውደጥናት መድረኮች በከተማ ልማት ዘርፍ ዙሪያ የሚታዩ መልካም አፈጻጸሞችና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል

የከተሞች የልምድ ልውውጥ አውደጥናት መድረኮች በከተማ ልማት ዘርፍ ዙሪያ የሚታዩ መልካም አፈጻጸሞችና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል

(ጥር 04 ቀን፣ 2016 ዓ.ም፣ ድሬዳዋ) የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚስቴር ጋር በመተባበር በማዘጋጃቤታዊ ገቢ ሪፎርም፣ በከተማ ፕላን አፈጻጸም፣ በመሬት አስተዳደር፣ ህጋዊ ካዳስተርና ጽዳትና ውበት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የልምድ ልውውጥ አውደ ጥናት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹና በዕቅድ የሚመሩ እንዲሁም የነዋሪዎቻቸውን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይሩ ለማድረግ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ  እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ፈንታ አያይዘው እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ከመሰረቱ ቀደምት ሃገራት መካከል አንዷ እንደመሆኗ መጠን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ካሪያ ቤላህራች ሞሮኮን በዓለም አቀፉ የሰላም ምክር ቤት ሊወክል ነው።

ካሪያ ቤላህራች ሞሮኮን በዓለም አቀፉ የሰላም ምክር ቤት ሊወክል ነው።

ለአለም አቀፍ ሰላም የሚሰሩትን የማክበር እና የማመስገን ፣የአለም አምባሳደሮችን እና የሰላም ተሟጋቾችን በማሰባሰብ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው የሰላም ምክር ቤት (ዩፒሲ) ፣ ሐሙስ ዕለት ዘካርያ ቤላራች የሞሮኮ አምባሳደር እና ተወካይ አድርጎ ሰይሟል። በዩፒሲ የሞሮኮ አምባሳደር ቤላህራች ሰላምን ለማስፋፋት ባሳዩት ልዩ ቁርጠኝነት እና በማህበረሰቦች መካከል ድልድይ ለመገንባት ላደረጉት የረጅም ጊዜ አስተዋጽኦ መመረጣቸው ታውቋል። ዘካርያ ቤላራች በዲፕሎማሲያዊ እና በማህበራዊ ዘርፎች ያለው ሰፊ ልምድ የ ሰላም ምክር ቤትን ሀሳቦች ለመወከል ትክክለኛውን ምርጫ ናቸው ተብሏል። ሹመቱን ሲቀበሉ ቤላህራች የ ዩፒሲ ፕሬዝዳንት እና መስራች የሆኑትን ሼክ ቃሲም ባድርን አመስግነዋል። የቤላህራች ተልእኮ ግንዛቤን ማሳደግ፣ ውይይትን ማመቻቸት እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የታቀዱ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሂውማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አላከበረችም ሲል ተቸ።

ሂውማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት አላከበረችም ሲል ተቸ።

ሂውማን ራይትስ ዎች አዲስ ባወጣው የዓለም የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት እና የአማራ ክልል ግጭትን የዳሰሰ ሲሆን በኢትዮጵያ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ወደሚያስችሉ ዓለማቀፋዊ ርምጃዎች አላመራም በማለት ተችቷል። በአማራና ትግራይ ክልሎች በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ሌሎች ጥሰቶች እስከአሁንም ቀጥለዋል ያለው ድርጅቱ፣ አውሮፓ ኅብረትና ሌሎች ምዕራባዊያን አገራት ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግንኙነታቸውን እንደገና ጀምረዋል በማለት ወቅሷል። የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ እንደሚያደናቅፉና በአማራ ክልልም ውጊያ፣ የቴሌኮምንኬሽን መቋረጥና በረድዔት ሠራተኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለዕርዳታ ሥርጭት እንቅፋት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጠቅሷል። በሚያዝያ ወር የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው  የፌደራል መንግስት የክልሉን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ቤተክርስቲያን ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ቤተክርስቲያን ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው ወቅታዊ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ እንዲሁም ከበዓላት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየታዩ ስላሉ ሃሰተኛ ወሬዎች ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች እንደገጠሟት የገለጹ ሲሆን ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች ብለዋል።ብፁዕነታቸው የማይደፈር ሲደፈር አይተናል ፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም ያሉ ሲሆን ቤተክርስቲያን በመንግስት እየታመነች አይደለም ሲሉ ተችተዋል።ባለፈው የተለያዩ አባቶች በተለያየ መንገድ ተናገሯቸው ስለተባሉት ጉዳዮች ተነስቶ መንግስት ቀየሜታውን ገልጾ ቤተክርስቲያን መልስ እንድትሠጥበት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነትን “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነትን “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

01/05/2016 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን  መግባቢያ ሰነድ “ያለልዩነት” የምንደግፍ መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመግለጫውም ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር በመምከር ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናቸውን ለመወጣት ፓርቲዎቹ ዝግጁ መሆናቸውን የጋራ ምክር ቤቱ ተአስታውቋል።ሶማሊያዊያን ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ስምምነት በመቃወም “ዋን ሚሊዮን ማርች” የተሰኘ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊንዱ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የገቡትን ስምምነት እየተቃወሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ስምምነትም የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር አይኖርም፤ የተጣሰ ሕግና የተሰበረ…
ተጨማሪ ያንብቡ