ሀገርኛ

ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

ከታገቱት 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች መሃከል ሶስቱ ተለቀቁ::

አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2016 የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ካገቷቸው ስድስት የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ፕሮጀክት ሠራተኞች መካከል ሦስቱ መለቀቃቸውን መናገሩን ዴይቸቨለ ዘግቧል። ከተለቀቁት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ኬንያዊ ነው ተብሏል።ቀሪዎቹን ታጋቾች የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠሉን ተቋሙ እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ ታጋቾቹ በምን አኳኋን እንደተለቀቁ ግን ተቋሙ አልገለጠም ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክት ሠራተኞች በተሽከርካሪ ሲጓዙ የታገቱት ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
ተጨማሪ ያንብቡ

በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአለም አቀፍ ፍ/ቤቶች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 በኢትዮጵያ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች መርማሪ ኮሚሽን አገራትና ተቋማት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤቶች ጭምር ተጠያቂ እንዲኾኑ ጥረት እንዲያደርጉ ረቡዕ'ለት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት ጠይቋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ኹኔታ መከታተሉንና ለጦርነቱ ተጎጂዎች ድጋፍ መስጠቱን እንዳያቋርጥም ኮሚሽኑ አሳስቧል። ኮሚሽኑ፣ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቀጠሉበት ወቅት ቆይታ ጊዜው እንዲያበቃ መደረጉ ስህተት መኾኑንም ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ገልጧል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበል ተናገረ፡፡

አርብ ጥቅምት 15 /2016 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ "ሐሰተኛ" ሪፖርት አውጥቷል በማለት ትናንት ማምሻውን ባወጣው ምላሽ ከሷል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉበት ወቅት ኮሚሽኑ ይህን ሪፖርት ማውጣቱ፣ "ኃላፊነት የጎደለው" እና "ዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ለማሳሳት ኾን ተብሎ የተሠራ" ነው በማለት ወቅሷል።የክልሉ አስተዳደር አያይዞም፣ ፌደራል መንግሥቱ ወደፊት ተመሳሳይ ሪፖርቶች እንዳይወጡ፣ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጎንደር ዲስትሪክቱን ወደ ሽሬ ለማድረግ የጀመረው እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጠመው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጎንደር ዲስትሪክቱን ወደ ሽሬ ለማድረግ የጀመረው እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጠመው

ጥቅምት 12/2016 የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎንደር ዲስትሪክት የነበረውን ወደ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ለማዞር የጀመረው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጿል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ውስጥ ሲሰጠው የነበረው አገልግሎት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ተቋርጦ ቆይቶ ነበር ብለዋል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ዲስትሪክቱን ጎንደር በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሆኖም፣ በአሁኑ ሰዓት በተቋሙ የተዘረጋው ሥርዓት ስራ ሊያጓትት የሚችልና በህዝብ ዘንድ ቅሬታን የሚያስነሳ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ወቅሰዋል፡፡ በአራቱም የአገልግሎት ማእከላት ማለትም ዳንሻ፣ ባህከር፣ አድረመጥ እና ሁመራ የሚገኙ የባለሙያዎችን ደሞዝ ጭምር ወደ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው ተነገረበዳግም ጌታቸው

ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው ተነገረበዳግም ጌታቸው

ጥቅምት 12/2016 በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን ለአዲስ ጊዜ ገለፁ፡፡አክሱም ከተማ በቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተች ከተማ መሆኗን የገለፁት ሀላፊው በጦርነቱ ከወደሙት ቅርሶች ባለፈ የተዘረፉና የጠፉ 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊው ጨምረው፣ የነዚህ ቅርሶች መጥፋት በከተማዋ የቱሪዝም እንቀስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አብራርተዋል፡፡የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ሀላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን እንደገለጹልን፣ ጽሕፈት ቤታቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
ዳግም የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፀጥታ ችግር እንቅፋት እንደሆነ

ዳግም የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፀጥታ ችግር እንቅፋት እንደሆነ

ጥቅምት 12/2016በጣና ሀይቅና በዙሪያው በድጋሚ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው የጣና ሀይቅ እና ሌሎች ውሀማ አካላት ኤጀንሲ ገልጿል።ሀሳባቸውን ለአዲስ ጊዜ የሰጡት የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ መልካሙ አዳም በበኩላቸው አረሙ መስፉፉቱን መመልከታቸዉን አንስተው ከዚህ ቀደም ችግሩን ለመከላከል ኮሚቴ መዋቀሩን ተናግረዋል።የጣና ሀይቅ እና ሌሎች ዉሀማ አካላት ኤጀንሲ ሀላፊው አቶ ፈንቴ አለም የእምቦጭ አረሙ ምን ያህል ሄክታር እንደተስፋፋ መረጃዉ እንደሌላቸው አንስተው ባለው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ችግሩን ለመቅረፍ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጋቸውን ገልፀዋል።ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የባሕር ዳር ነዋሪዎች እንደነገሩን እየተስፋፋ የመጣው አረም በአፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው የሀይቁ ቱሪዝም ላይ እክል እንዳይሆን ስጋት እንዳደረባቸው አንስተዋል።እንደከዚህ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ተነገረ

በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ተነገረ

ሰኞ ጥቅምት 12/2016   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ አዲስ ባወጣው የሩብ ዓመት ሁኔታዊ ሪፖርት በኢትዮጵያ 8 ሺህ 552 ያህል ትምህርት ቤቶች በሙሉ እና በከፊል ዝግ መሆናቸውን ገልጿል። በዚህም 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጨ መሆናቸውን አስታውቋል። የትምህርት ቤቶቹ መዘጋትም ሆነ የህጻናቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆን በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ችግር መሆኑን የጠቆመው የዩኒሴፍ ሪፖርት በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት ለችግሩ መስፋፋት በቀዳሚነት የተቀመጠ ምክንያት ሆኗል። በዩኒሴፍ የተቀመጠው በሙሉ እና በከፊል የተዘጉ ትምህርት ቤቶች አሀዝ ሀያ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ቁጥር እንደሚሸፍን ሪፖርቱ በማብራሪያው ላይ አስቀምጧል። ድርጅቱ በማጠቃለያው ላይ ጊዜው…
ተጨማሪ ያንብቡ
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የአማራ ክልል ግጭት ለስራዬ እንቅፋት ሆኖብኛል አለ

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የአማራ ክልል ግጭት ለስራዬ እንቅፋት ሆኖብኛል አለ

ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም   የዓለም የምግብ ፕሮግራም ትናንት ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ለማቀርበው የምግብ እርዳታ የአማራ ክልል ግጭት እና የገንዘብ እጥረት ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል ሲል አስታወቀ። የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአማራ ክልል በዘጠኝ ዞኖች በአሁኑ ወቅት በትጥቅ የተደገፈ ከፍተኛ ግጭት በመኖሩ እንቅስቃሴው መገደቡን እና በክልሉ የሚገኙ ሰራተኞቹን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ንብረቶቹ እንዳይዘረፉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን  አስታውቋል። በተጨማሪም፣ እስከ አመቱ አጋማሽ ድረስ የረድኤት አቅርቦቱን በአግባቡ ለማከናወን ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ 219 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እጥረት እንደገጠመው የገለጸው ድርጅቱ በዚህም ሳቢያ በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ 50 በመቶ ለሚሆኑት ብቻ ለማቅረብ መገደዱን ጠቁሟል። እስከ ጥቅምት መጨረሻ ድረስ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በእገታ ስጋት ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ነው

በእገታ ስጋት ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ነው

ጥቅምት 10/2016   ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች በታጣቂዎች እንደታገቱ የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ አጋቾቹ የያዟቸውን ሰዎች ለመልቀቅ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቁ የተነገረ ሲኾን ከድርጊቱ መደጋገም የተነሣ ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው የገለጹ ነዋሪዎችም ቀዬአቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ እገታ ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች በአንዳቸው እንደተወለዱ የሚናገሩትና ስለኹኔታው እንደሚያውቁ የሚገልጹት አስተያየት ሰጪ፣ ሰሞኑን ስምንት አርሶ አደሮች በነፍስ ወከፍ እስከ 300ሺሕ ብር የማስለቀቂያ ዋስትና እንደከፈሉ ተናግረዋል፡፡ ከእገታው የተለቀቁ አንድ ግለሰብ ደግሞ፣ ነጻ ለመውጣት ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋራ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለናል ሲሉ ለዜና ማሰራጫዎች ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ኃይሉ አዱኛ፣ መንግሥት ኦነግ…
ተጨማሪ ያንብቡ