አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2016
የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ካገቷቸው ስድስት የአሉቶ የእንፋሎት ኃይል ፕሮጀክት ሠራተኞች መካከል ሦስቱ መለቀቃቸውን መናገሩን ዴይቸቨለ ዘግቧል።
ከተለቀቁት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ኬንያዊ ነው ተብሏል።ቀሪዎቹን ታጋቾች የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠሉን ተቋሙ እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ ታጋቾቹ በምን አኳኋን እንደተለቀቁ ግን ተቋሙ አልገለጠም ብሏል።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክት ሠራተኞች በተሽከርካሪ ሲጓዙ የታገቱት ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
