ሀገርኛ

“ዝክረ የኢትዮጵያ አብዮት ”በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ

“ዝክረ የኢትዮጵያ አብዮት ”በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ

እታገኘሁ መኮነን የካቲት  13/2016 የኢትዮጵያ አብዮት እነሆ ሃምሳ አመት ደፈነ፡፡ በዚህ ሃምሳ ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ  ለታዩ የፖለቲካ ከፍታና ዝቅታዎች  አብዮቱ ምን አበረከተ ? ሲል ለመጠየቅ እና ለማወያየት መዘጋጀቱን ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) ባሳለፍነው ሰኞ የካቲት 11/2016 ለመገናኛ ብዙሃን  በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ‹‹ከየካቲት እስከ የካቲት›› በሚል ርዕስ  በስድስት ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የውይይት መድረክ ከያዝነው የካቲት ወር ማብቂያ  ጀምሮ በየሁለት ወሩ  ለማካሄድ መዘጋጀታቸውን የተናገሩት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የራስ ወርቅ አድማሴ (ዶር ) ናቸው፡፡የአብዮቱ መሰረታዊ ጥያቄ መልስ አግኝቷል ወይስ አላገኘም  ? አገሪቱንስ ወዴት አቅጣጫ ወሰዷት ? የመሬት ለአራሹ አዋጅ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
በሶማሌ ክልል የተገነባው ጎዴኡጋዝ አየር ማረፊያ ዛሬ ተመረቀ

በሶማሌ ክልል የተገነባው ጎዴኡጋዝ አየር ማረፊያ ዛሬ ተመረቀ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን የክልሉ ኮምንኬሽን አስታውቋል። አውሮፕላን ማረፊያው በአንድ ጊዜ አራት ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ማስተናገድ እንደሚችል ቢሮው ገልጧል። ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት፣ አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐሃዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያውን ተርሚናል ግንባታ ያከናወነው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ
በአማራ ክልል መርዓዊ አካባቢ ንጹሀን ዜጎች “ግድያ” በገለልተኛ አካል ይመርመር ሲል የአሜሪካ መንግስት ጠየቀ

በአማራ ክልል መርዓዊ አካባቢ ንጹሀን ዜጎች “ግድያ” በገለልተኛ አካል ይመርመር ሲል የአሜሪካ መንግስት ጠየቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ የአሜሪካ መንግስት በአማራ ክልል መርዓዊ አካባቢ ንጹሀን ተገድለዋል መባሉ እንዳሳሰበው አስታወቁ። የአሜሪካ መንግስት በአማራ ክልል ተፈጽሟል የተባለው የንጹሀን ግድያ በገለልተኛ አካላት እንዲመረመር እንዲሁም ለሰብዓዊ መብት መረጃ ስብሰባ ያልተገደበ ስርዓት እንዲኖር አጽንዖት ሰጥቷል። በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመንግስት ኃይሎች እና ታጣቂዎች የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመግታት "ከግጭት ይልቅ መነጋገር" የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተናገሩት።
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ  የሃይማኖት  ተቋማት ጉባኤ መንግስት ግብረ ሰዶማዊነትን መብትን የሚፈቅድ  የሳሞአ ስምምነት መፈረሙን እቃወማለው አለ

የኢትዮጵያ  የሃይማኖት  ተቋማት ጉባኤ መንግስት ግብረ ሰዶማዊነትን መብትን የሚፈቅድ  የሳሞአ ስምምነት መፈረሙን እቃወማለው አለ

የካቲት 1/2016 የኢትዮጵያ  የሃይማኖት  ተቋማት ጉባኤ  ዛሬ በሰጠው መግለጫ  በአውሮጳፓ ህብረት እና በአፍሪካ ፣በካሪቢያንና በፓስፊክ  ሀገራት ለ 20 አመታት እንዲዘልቅ ታሳቢ ተደርጎ የተከናወነው  የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር  በውስጡ  ከኢትዮጵያ ህዝብ  የሃይማኖትና የባህል እሴቶች ጋር የሚፃረሩ ፅንሰ ሀሳቦችና  ትርጎሞች  ስላለው የሳሞአ ስምምነትን ያደረገው  የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን እንዲሰረዝ  ጠይቋል። ጉበኤው በስምምነቱ  ግብረሰዶም  ፣ ፆታ መቀየር ፣ ውርጃ  እና ሁሉና ዓቀፍ  ግልሙትናን  ህጋዊ  የማድረግ አንቀጾች ተካተዋል ብሏል። በተጨማሪ   እጅግ አደገኛ  ይዘት ያለው  ለአህጉሪቱ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት  አስገዳጅ በሆነ መንገድ  እንዲሰጥ የሚል ነጥብ ተካቷል ይሄም የኢትዮጰያን ባህል ክፉኛ የሚጎዳ ነው ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ
አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው ተሾሙ። አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው ተሾሙ። አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ም/ጠ/ሚኒስትርነት እና የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት አጽድቋል። ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአቶ ተመስገን ጥሩነህን እና የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቶቹን አጽድቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
”በመቶ የሚቆጠሩ እስረኞች ብቻ ናቸው ያሉት ” ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

”በመቶ የሚቆጠሩ እስረኞች ብቻ ናቸው ያሉት ” ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

ትናንት በህዝብተወካዮች ም/ቤት  የኢትዮጵያን የፀጥታ ሁኔታበሚመለከት ማብራሪያ ያቀረቡት ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩት አካላት  የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ልምምድ የሌላቸው ናቸው ሲሉ የተቹ ሲሆን ከሸኔ ጋር በታንዛንያ የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት ምንም ለህዝብ ይፋ ማድረግ የተቻለ ነገር የለም ብለዋል፡፡ በአማራ ክልል የሚታየውን አለመረጋጋት በተመለከተ የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ልማት፣ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እና የወሰን ጉዳዮች ናቸው ያሉ ሲሆን ከሰላም ማስከበር ጋር በተያያዘ ግን መንግሥት በቀጣይነት ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለውን ጉዳይ አንስማማም አንቀበልም አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን ሕግ ለማስከበር እንሰራለን  ሲሉ አክለዋል። "ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ባንኩ  በአፍሪካ ትልቁን ያልተነካ ገበያ እየፈለገ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሁለት ሳምንት በኃላ ከውጭ የፋይናንስ ተቋማት የኢንቨስትመንት የባንክ ፍቃድ ማመልከቻዎችን እንደሚቀበል በመግለፁ  ጥሪውን ተቀብሎ ፍቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት ዝቅተኛው የተከፈለ ካፒታል ለዉጪ ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር እና ከባንክ ላልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት 25 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው ይገባል። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ በኢትዮጵያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በትግራይ ክልል፣ ሰሜን ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች  የተበላሸ ፣መጥፎ ጠረን ያለው እና የነቀዘ ዱቄት ከለጋሽ ደርጅቶች መታደላቸውን ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል፣ ሰሜን ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች የተበላሸ ፣መጥፎ ጠረን ያለው እና የነቀዘ ዱቄት ከለጋሽ ደርጅቶች መታደላቸውን ገልጸዋል።

22/05/16 ላለፉት 13 ወራት የረባ ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁት ተፈናቃዮቹ ፤ ከረጅም ጊዚያት በኃላ ጥር 20/2016 ዓ.ም መሰጠት የተጀመረው ዱቄት ጥራት የሌለው ፣ የተበላሽ ፣ የነቀዘና መጥፎ ጥረን ያለው መሆኑ በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል።  የቴሌቪዥን ጣቢያው " ለተፈናቃዮቹ የተሰጠው ዱቄት ለምግብነት ቢያውሉት ለጤናቸው ጠንቅ እንደሚሆን የምግብ ባለሙያዎች አረጋግጠውልኛል " ብሏል።   ዱቄቱ በእርዳታ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች 'ተበላሸ' ስለተባለው እህል ምላሽ እንዲሰጡ የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ጉዳዩ በጥብቅ እየተከታተለው መሆኑ የገለፀው የእንዳስላሰ ሽረ መንግስታዊ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ፤  ዱቄቱ ያከፋፈሉ ለጋሽ ድርጅቶች ያደሉት እንዲሰበስቡና ማደል እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ መፃፉን አስታውቋል። ፅህፈት ቤቱ ለለጋሽ ድርጅቶች በፃፈው…
ተጨማሪ ያንብቡ
ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስና መባባሱን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ

ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስና መባባሱን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ

22/05/2016 በተጠናቀቀው የፈረንጆች 2023 ዓመት በኢትዮጵያ የሙስና ወንጀሎች መጨመራቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። የ180 አገራት የሙስና ነክ ወንጀሎችን በየዓመቱ የሚመዝነው ተቋም ይፋ ባደረገው የ2023 ሙሉ ዓመት ሪፖርት ኢትዮጵያ በመመዘኛዎቹ 37 ከ100 ነጥብ በማግኘት 98ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ በተቋሙ መለከያ መሰረት ዓለም አቀፍ አማካኝ የሙስና ውጤት 43 ነጥብ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከአማካኝ በታች በስድስት ነጥብ ዝቅ ብላ ትገኛለች። በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ነጥብ አሰጣጥ መሰረት 100 ማለት ከሙስና ነጻ ማለት ሲሆን ወደ ዜሮ እየቀነሰ ሲሄድ የሙስና ወንጀሎች መጨመራቸውን አመላካች ነው። ተቋሙ የሚፈትሻቸው የሙስና ዓይነቶች ጉቦ፣ በጀቶችን ማዞር፣ የመንግሥት ስልጣንን ያለከልካይ ለግል ጥቅም ማዋል፣ የመንግስት አካላት በመንግስት ዘርፍ ሙስናን የመቆጣጠር ችሎታ፣ በመንግስት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ፍላጎታቸውን “በነፍጥ ማስፈጸም” በሚፈልጉ ኃይሎች ላይ፤ ህግ የማስከበር እርምጃ “ተጠናክሮ” እንደሚቀጥል ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ

ፍላጎታቸውን “በነፍጥ ማስፈጸም” በሚፈልጉ ኃይሎች ላይ፤ ህግ የማስከበር እርምጃ “ተጠናክሮ” እንደሚቀጥል ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ

17/05/17 ገዢው ብልጽግና ፓርቲ “በነፍጥ ፍላጎታቸውን የማስፈጸም ዓላማ አላቸው” ያላቸው አካላት ላይ፣ “ህግን የማስከበር ስራ” “በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድ” ውሳኔ ማስተላለፉን አስታወቀ። በሀገሪቱ የተሟላ ሰላም ለማስፈን፤ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ “ሰላማዊ አማራጮች” ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መወሰኑንም ገልጿል። ብልጽግና ፓርቲ ይህን ያስታወቀው ካለፈው ሰኞ ጥር 13፤ 2016 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ያካሄዳቸውን የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎችን ሲያጠናቀቅ ባወጣው መግለጫ ነው። በሁለቱ ሰብሰባዎች ላይ “አበይት ሀገራዊ ጉዳዮች እና ልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች” ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ፓርቲው በስብሰባዎቹ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ የሚመለከተው ይገኝበታል። “በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት” የተፈጠሩ “ትስስሮች” አስከትለዋቸዋል የተባሉ ግጭቶች፤…
ተጨማሪ ያንብቡ