አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው ተሾሙ። አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ም/ጠ/ሚኒስትርነት እና የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት አጽድቋል።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአቶ ተመስገን ጥሩነህን እና የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቶቹን አጽድቋል።