የኢትዮጵያ  የሃይማኖት  ተቋማት ጉባኤ መንግስት ግብረ ሰዶማዊነትን መብትን የሚፈቅድ  የሳሞአ ስምምነት መፈረሙን እቃወማለው አለ

የካቲት 1/2016

የኢትዮጵያ  የሃይማኖት  ተቋማት ጉባኤ  ዛሬ በሰጠው መግለጫ  በአውሮጳፓ ህብረት እና በአፍሪካ ፣በካሪቢያንና በፓስፊክ  ሀገራት ለ 20 አመታት እንዲዘልቅ ታሳቢ ተደርጎ የተከናወነው  የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር  በውስጡ  ከኢትዮጵያ ህዝብ  የሃይማኖትና የባህል እሴቶች ጋር የሚፃረሩ ፅንሰ ሀሳቦችና  ትርጎሞች  ስላለው የሳሞአ ስምምነትን ያደረገው  የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን እንዲሰረዝ  ጠይቋል።

ጉበኤው በስምምነቱ  ግብረሰዶም  ፣ ፆታ መቀየር ፣ ውርጃ  እና ሁሉና ዓቀፍ  ግልሙትናን  ህጋዊ  የማድረግ አንቀጾች ተካተዋል ብሏል።

በተጨማሪ   እጅግ አደገኛ  ይዘት ያለው  ለአህጉሪቱ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት  አስገዳጅ በሆነ መንገድ  እንዲሰጥ የሚል ነጥብ ተካቷል ይሄም የኢትዮጰያን ባህል ክፉኛ የሚጎዳ ነው ብሏል።