በአማራ ክልል መርዓዊ አካባቢ ንጹሀን ዜጎች “ግድያ” በገለልተኛ አካል ይመርመር ሲል የአሜሪካ መንግስት ጠየቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ የአሜሪካ መንግስት በአማራ ክልል መርዓዊ አካባቢ ንጹሀን ተገድለዋል መባሉ እንዳሳሰበው አስታወቁ።

የአሜሪካ መንግስት በአማራ ክልል ተፈጽሟል የተባለው የንጹሀን ግድያ በገለልተኛ አካላት እንዲመረመር እንዲሁም ለሰብዓዊ መብት መረጃ ስብሰባ ያልተገደበ ስርዓት እንዲኖር አጽንዖት ሰጥቷል።

በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመንግስት ኃይሎች እና ታጣቂዎች የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመግታት “ከግጭት ይልቅ መነጋገር” የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተናገሩት።