በሶማሌ ክልል የተገነባው ጎዴኡጋዝ አየር ማረፊያ ዛሬ ተመረቀ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን የክልሉ ኮምንኬሽን አስታውቋል። አውሮፕላን ማረፊያው በአንድ ጊዜ አራት ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ማስተናገድ እንደሚችል ቢሮው ገልጧል። ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት፣ አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐሃዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያውን ተርሚናል ግንባታ ያከናወነው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።