“ዝክረ የኢትዮጵያ አብዮት ”በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ
እታገኘሁ መኮነን የካቲት 13/2016 የኢትዮጵያ አብዮት እነሆ ሃምሳ አመት ደፈነ፡፡ በዚህ ሃምሳ ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ ለታዩ የፖለቲካ ከፍታና ዝቅታዎች አብዮቱ ምን አበረከተ ? ሲል ለመጠየቅ እና ለማወያየት መዘጋጀቱን ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) ባሳለፍነው ሰኞ የካቲት 11/2016 ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ‹‹ከየካቲት እስከ የካቲት›› በሚል ርዕስ በስድስት ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የውይይት መድረክ ከያዝነው የካቲት ወር ማብቂያ ጀምሮ በየሁለት ወሩ ለማካሄድ መዘጋጀታቸውን የተናገሩት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የራስ ወርቅ አድማሴ (ዶር ) ናቸው፡፡የአብዮቱ መሰረታዊ ጥያቄ መልስ አግኝቷል ወይስ አላገኘም ? አገሪቱንስ ወዴት አቅጣጫ ወሰዷት ? የመሬት ለአራሹ አዋጅ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን…
