የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “አሳፋሪ” የምርመራ ሂደት እየተከተለ ነው – ኦነግ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው መግለጫ የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት በቴ ኡርጌሳ ግድያን በተመለከተ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “አሳፋሪ” የምርመራ ሂደት እየተከተለ ነው ሲል ተናገረ ። ኦነግ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ፤ ግንባሩ በመንግስት በኩል የሚደረገው “ምርመራ ተዓማነት የጎደለው ፣ የማስረጃ ችግር እና ሀሰተኛ ማስረጃዎችም የቀረቡበት ነው ሲል ተችቷል፡፡ ስለዚህም በባቲ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የሚደረገው ምርመራ እየተባለ የሚጠራው መረጃ ከጅምሩ ሆን ተብሎ በተዘበራረቁ በርካታ ማስረጃዎች፣ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የሀሰት ዘመቻዎች የተበላሸ መሆኑን ደግመን እንገልፃለን። ሁኔታው በደርግ ጊዜ የነበረውን የቀይ ሽብር ወቅትን ይመስላሉ ሲል ኦነግ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በቴ ኡርጌሳ ከእንግዳ ማረፊያው ሲወሰድ የተመለከቱ አንድ የጥበቃ ሰራተኛ ከክስተቱ…
