”በመቶ የሚቆጠሩ እስረኞች ብቻ ናቸው ያሉት ” ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ትናንት በህዝብተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያን የፀጥታ ሁኔታበሚመለከት ማብራሪያ ያቀረቡት ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩት አካላት የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ልምምድ የሌላቸው ናቸው ሲሉ የተቹ ሲሆን ከሸኔ ጋር በታንዛንያ የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት ምንም ለህዝብ ይፋ ማድረግ የተቻለ ነገር የለም ብለዋል፡፡ በአማራ ክልል የሚታየውን አለመረጋጋት በተመለከተ የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ልማት፣ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እና የወሰን ጉዳዮች ናቸው ያሉ ሲሆን ከሰላም ማስከበር ጋር በተያያዘ ግን መንግሥት በቀጣይነት ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። እጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ የሚለውን ጉዳይ አንስማማም አንቀበልም አናደርግም። መንግሥት ነን አቅም በፈቀደ መጠን ሕግ ለማስከበር እንሰራለን ሲሉ አክለዋል። "ሕግ ለማስከበር ስንሰራ በየአንዳንዷ ሰከንድ…
