አዲስ ጊዜ

230 Posts
በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚኖረው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – ሚቲዎሮሎጂ

በሚቀጥሉት 20 ቀናት በሚጥለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት እና የወንዞች ሙላት ሊያጋጥም ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ። በሚቀጥሉት 10 ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በዓባይ፣ ተከዜ፣ ባሮአኮቦ፣ ኦሞ፣ ጊቤ፣ አዋሽ፣ አፋር ደናክል፣ የላይኛውና የመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የላይኛው የገናሌ ዳዋና ዋቤ ሸበሌ ተፋሰሶች መካከለኛና በጣም ከፍተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተትና መሰንጠቅ፣ እንዲሁም የሰብል በጎርፍ የመጠረግ ሁኔታዎች እንዳይኖር መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል። እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎችም የሰብል በሽታ እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁሟል። በተጨማሪም በሚቀጥሉት 8 ቀናት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

ጋዜጠኞች ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት ጥብቅና የሚቆም እና የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጥ የጋዜጠኞች  እና የሕግ ባለሙያዎች ጥምረት ሊመሰረት ነው፡፡

እታገኘሁ መኮነን MELA ( Media Lawyers alliance )ተብሎ የተሰየመው ይህ የሚዲያ እና የህግ ባለሞያዎች ጥምረት በምስረታ ሂደት ላይ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) ሰምተናል፡፡ ኅብረቱ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመሆን  በጥምረቱ ዙሪያ  ትናንት ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ)  ዳሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ ጥምረቱ  የጋዜጠኝነት ሙያ ማህበራትን ማገዝ፣ጋዜጠኞች በሰሩት ስራ ለሚያጋጥማቸው የመብት ጥሰት እና ጫና የሕግ ድጋፍ የመሰጠት፣ለጋዜጠኞች መታሰር ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር የማድረግ፣ በመገናኛ ብዙኃን ዙሪያ  ህጎች ሲወጡ በባለሞያዎች ጥናት ማስጠናት እና ግብዓት ማቅረብ እንዲሁም በሚዲያው ህብረተሰብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

 በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች አስቸኳይ ፍትህ እንዲያገኙ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።

ማህበሩ የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደትም ከፖለቲካ አተያይ በፀዳ መንገድ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር አዲስ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በአዲስ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን መጎብኘታቸውን ትናንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ስለ ማረሚያ ቤት አያያዝ እና አጠቃላይ የፍትህ ሂደቱ ያለበትን ሁኔታ ከጋዜጠኞቹ ጋር እንደተወያዩ ማህበሩ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር በተያዙበት ወቅት የተያዙበት መንገድም ሆነ ከተያዙ በኃላ ያለው የፍርድ ቤት ሂደት አግባብነት እንደሚጎድለው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱም ማረሚያ ቤቶች ከሁለት ዓመት በላይ ሳይፈረድባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞች መኖራቸውን ማኅበሩ እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ስለሆነም በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የሚዲያ ምህዳሩ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የቅድመ መደበኛ ስርዓተ ትምህርት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት        ይፋ ሆነ

የቅድመ መደበኛ ስርዓተ ትምህርት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ

ችልድረን ብሊቭ  ህጻናትን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰብን  በአለም አቀፍ ደረጃ ለማብቃት የሚሰራ  አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ድርጅቱ ድህነትን እና ኢፍትሃዊነትን በማሸነፍ ላይ ያተኮረ ተልእኮ በመያዝ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ  ህፃናት ፣ በራስ መተማመንን እና የራሳቸውን የወደፊት ህይወት ለመቅረጽ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ይሰራል፡፡ችልድረን ብሊቭ  የቻይልድ ፈንድ አሊያንስ አባል ነው፡፡ ቻይልድ ፈንድ በ70 ሃገራት  ወደ 36 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናትን እና ቤተሰቦቻቸውን በጋራ የሚደግፍ ዓለም አቀፍ ኔትወርክ ነው፡፡ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረው ድርጅቱ  እንደ ቅድመ ልጅነት እንክብካቤ እና ልማት ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና እና ስነ-ምግብ ፣  የወጣቶች ስራ ስምሪት ላይ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡   እ.ኤ.አ. በ…
ተጨማሪ ያንብቡ
‹‹በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል›› – አቶ አበባው ደሳለው፤ የአብን የፓርላማ አባል          ‹‹ምክር ስንለግስ ቀለል አድርገው የሄዱ ሰዎች በኋላ ዋጋ ይከፍላሉ።››ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

‹‹በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል›› – አቶ አበባው ደሳለው፤ የአብን የፓርላማ አባል ‹‹ምክር ስንለግስ ቀለል አድርገው የሄዱ ሰዎች በኋላ ዋጋ ይከፍላሉ።››ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባል የሆኑት  አቶ አበባው ደሳለው፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ባለፉት 10 ወራት “የጅምላ ግድያ” ጨምሮ   “ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል”  ብለዋል፡፡ በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች “ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” ያሉት አቶ አበባው  ለማሳያነትም በእርሳቸው ምርጫ ክልል ጅጋ፣ በፍኖተሰላም፣ በመርዓዊ፣ በደብረ ኤልያስ፣ በደብረሲና፣ ጎንደር እና ወሎ ተፈጽመዋል ያሏቸውን ግድያዎች ጠቅሰዋል። ጾታዊ ጥቃት እና ድብደባን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውንም  አመልክተዋል። በአማራ ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ያሉትን “የጅምላ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በቱርክ የተገናኙት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አለመግባባቶችን በሰላም እንደሚፈቱ ገለጹ

በቱርክ የተገናኙት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አለመግባባቶችን በሰላም እንደሚፈቱ ገለጹ

ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ኢትዮጵያ  ከስድስት ወራት በፊት  የባህር በር መግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ነበር ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ  ውዝግብ ውስጥ የገቡት፡፡ በዚህም ምክንያት ሰኔ 24/ 2016 ዓ.ም በቱርክ ጋባዥነት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሃላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ለመነጋገር  ወደ ቱርክ   አንካራ ያቀኑት ኢትዮጵያና ሶማሊያ  በመካከላቸው ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም ከውይይታቸው በኋላ በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው ይህንን ያስታወቁት። በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አመቻችነት የተገናኙት የሁለቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች  ያላቸውን ልዩነቶች ለሁለቱም ተቀባይነት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአገራዊ ምክክር ሒደቱ በትግራይ ክልል እንዲጀመር ጥያቄ  ቀረበ

የአገራዊ ምክክር ሒደቱ በትግራይ ክልል እንዲጀመር ጥያቄ  ቀረበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረበውን የሥራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫ በማስመልከት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ውይይት  አድርጓል፡፡ በውይይቱም  የምክር ቤቱ አባላት በትግራይ ክልል የሃገራዊ ምክክር ሒደት እንዲጀመር ጠይቀዋል፡፡  ለምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር)፣ ከትግራይ ክልል ውጪ የአማራ ክልልን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተባባሪዎች ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የተሳታፊ ልየታና መረጣ ባሉት ነባራዊ ሁኔታዎች ምክንያት በአማራና በትግራይ ክልሎች አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡  በአማራ ክልል ባለው ግት ምክንያት 800 ያህል ለሚሆኑ ተባባሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ200 ያህሉ ብቻ መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡ በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ምንም ዓይነት ሥራዎችን…
ተጨማሪ ያንብቡ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ሊደረግ የነበረው “ቀሪ ምርጫ” ዛሬ እየተከናወነ ነው፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ሊደረግ የነበረው “ቀሪ ምርጫ” ዛሬ እየተከናወነ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው  ሃገራዊ ምርጫ በወቅቱ ባልተከናወነባቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ትናንት እሁድ ሰኔ 16፤ 2016 ምርጫ ሲካሄድ ውሏል።  የምርጫው መርሃ ግብር፤ ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንባቸው ቦታዎችንም ያካተተ ነበር። ሆኖም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች በትናንትናው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የ“ቀሪ ምርጫ” ሂደት ለዛሬ ተላልፏል። ቦርዱ “አንሻ ገብርኤል” እና “ገንገን” በተባሉ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ማካሄድ ያልቻለው የምርጫ ቁሳቁሶች በጊዜ ባለመድረሳቸው መሆኑን ገልጿል። ምርጫ ቦርድ “ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ” ለማድረግ አቅዶ የነበረው በ1,258 የምርጫ ጣቢያዎች ቢሆንም፤ የዛሬው የድምጽ መስጠት ሂደት የተከናወነው በ1,218 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ   በሰጡት ጋዜጣዊ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሳፋሪኮም እና ገበያ ኩባንያ የኢትዮጵያን የሥራ ፈጠራ ሥነ ምህዳር በእጅጉ የሚያሳድግ “ታለንት ክላውድ” ጀመሩ

ሳፋሪኮም እና ገበያ ኩባንያ የኢትዮጵያን የሥራ ፈጠራ ሥነ ምህዳር በእጅጉ የሚያሳድግ “ታለንት ክላውድ” ጀመሩ

ሳፋሪኮም ከገበያ ኩባንያ ጋር በአጋርነት፣ እንዲሁም የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ድጋፍ ታክሎበት  “ሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል። ፕሮግራሙ የመረጃ መረብን በመጠቀም የሥራ ዕድልን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። ፕሮግራሙ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነና ቀጣዩን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የዲጅታሉ ዓለም መሪዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህ የተለየ አሠራርን ይዞ የመጣው ፕላትፎርም እስከ 2024 እ.ኤ.አ ማብቂያ ድረስ፣ ለ10 ሺሕ ልዩ ልዩ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች አጠቃላይ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የሥራ ጉዟቸውን ማሳደጊያ ዕድሎችን የሚያቀርብ ነው። ይህንን በማድረግ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ኢንዱስትሪ ዕድገት የገታውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እጥረት ለመቅረፍ ፕሮግራሙ ዒላማ ያደርጋል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና…
ተጨማሪ ያንብቡ
በምዕራብ  ጎጃም ዞን ጅጋ ከተማ 18 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ

በምዕራብ  ጎጃም ዞን ጅጋ ከተማ 18 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ

የጸጥታ ሀይሎቹ የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ በመዝናናት ላይ የነበሩ የባንክ ሰራተኞችን እና መምህራንን ገድለዋል በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ፤ ቢያንስ 18 ሰዎች “በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን” ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ብሔራዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ “በአካባቢው ጥቃት ተፈጽሟል” የሚል መረጃ እንደደረሰው ገልጾ ፤ ክስተቱን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። የዓይን እማኞቹ፤ የጅጋ ከተማ ነዋሪዎች የተገደሉበት ክስተት የተፈጸመው ባሳለፍነው እሁድ ሰኔ 9፤ 2016 አመሻሽ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ዕለት ምሽት 11 ሰዓት ገደማ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ “ሶስት ፓትሮል” ተሽከርካሪዎች ከደንበጫ ወደ ጅጋ ከተማ እየገቡ በነበረበት ወቅት፤ “በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት” ከፊት በነበረው መኪና ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ መሸሻቸውን…
ተጨማሪ ያንብቡ