የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “የአማራ ታጣቂዎች” ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል ተናገረ
በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ታደሰ ወረደ ተናገሩ። አቶ ታደሰ “የመጀመሪያው እርምጃ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችን ማፍረስ እና የተቋቋሙትን ህገ-መንግስታዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ማፍረስ ሲሆን "የፍትህ ስርዓቱን ወደነበረበት መመለስ" በተከታይነት ይሰራል ብለዋል። ጄኔራሉ የታጠቁ ሃይሎች ከፌዴራል ሃይሎች ጋር መጠነኛ ግጭት በመፍጠር ሂደቱን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንም አብራርተው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግጭት እንዳያገረሽ በሚከላከል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት የፕሪቶሪያ ስምምነት የግዛትን ጨምሮ ሁሉም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለባቸው መደንገጉን አስታውሰዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ግን ትናንት በማህበራዊ ትስስር…
