በጎጃም ቡሬ ከተማ አቅራቢያ ግጭት መኖሩ ተነገረ
ሐሙስ ጥቅምት 08/2016 ካለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል እየሰፋ የመጣው ግጭት በተለይ በጎጃም አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉን አዲስ ጊዜ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ አንፃራዊ ሰላም ካለባቸው ከተሞች ውጭ በመከላከያ ሰራዊቱ እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል ያለው ግጭት አሁንም በበርካታ የገጠር ቀበሌዎች መኖሩን እኚሁ ነዋሪዎች አረጋግጠውልናል፡፡ ሰዓት እየጠበቁ የሚሰሙት የከባድ መሳሪያ የተኩስ ድምፆች የረጋ ሕይወት እንዳይኖራቸው ምክንያት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ምስክርነታቸውን ለአዲስ ጊዜ የሰጡት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ "ቡሬ ከተማ ላይ ጊዜያዊ ሰላም ቢኖርም ትናንት ከከተማው በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኝ ሸንዲ ከተማ አጠገብ ካለው ሰባ አዳር የሚባል አካባቢ ዙርያ ከባድ የተኩስ…
