ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው
ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን ከተለያዩ ምንጮች መረጃ አግኝቻለሁ በማለት ዋዜማ ዘግቧል፡፡ ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል ብሏል ዋዜማ በዘገባው። ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም። አሁን እየተደረገ ባለው…
