ቦሌ የሚገኘው ፉድ ዞን ሬስቶራንት የእሳት አደጋ ደረሰበት
አርብ ጥቅምት 09/2016 በአሸናፊ አሰበ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ6 ልዩ ስሙ ብራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ፉድ ዞን ሬስቶራንት ሀሙስ ምሽት 4 ሰዓት ከ40 ላይ ኩሽና ውስጥ ከመጥበሻ ላይ ተነሳ በተባለ እሳት ጉዳት እንደደረሰበት የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዲስ ጊዜ ገልጸዋል፡፡ በአደጋው ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን 1 ሰዓት 30 በፈጀ ርብርብ እሳቱን ወደሌላ ቦታ ሳይዛመት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ውስጥ ለማዋል መቻሉን ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ አደጋውን ለመቆጣጠር 25 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና 4 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት…
