አዲስ ጊዜ

230 Posts
የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ

የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ

የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ሲል የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ እንደ አገልግሎቱ መረጃ የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት 28.3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች(food items) 30 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 26 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል፡፡ በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በጥቅምት ወር ከነበረበት 29.2 በመቶ ወደ 28.3 በመቶ መቀነሱን መረጃው ያሳያል ማለቱን ከአገልግሎቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሸ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ

4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሸ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ

10/04/16 አሸናፊ አሰበ ኢትዮጵያ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት በመፍታት ሁሉን ተጠቃሚ ያደረገ ስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ብታሳይም ግብጽ በግድቡ ላይ እስካኹን በተደረጉት ድርድሮች ባራመደችው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ ቀርቷል ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገለጸ። በግድቡ የውሃ አሞላል ላይ እና በግድቡ አስተዳደር ላይ ኢትዮጵያ ለድርድር የተቀመጠችው ከሀገራቱ ጋር መተማመን ማስፈን እንጂ የሀገሪቱን በአባይ ውሃ ላይ የመጠቀም እና የመልማት መብት ለመገደብ አይደለም ሲል አቋሙን ያንጸባረቀው መግለጫው ኢትዮጵያ አሁንም በግልጽ ማስቀመጥ የምትፈልገው ዋነኛ ጉዳይ የአሁኑን እና የቀጣዩን የሀገሪቱን ትውልድ ተጠቃሚ በሚያደርግ እና የእኩልነትና ምክንያታዊነት መርሆችን ባከበረ አኳኋን የወንዙን ውሃ መጠቀሟን ትቀጥላለች ብሏል። አራተኛው…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር እንዲነጋገር ጥሪ ቀረበ።

መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር እንዲነጋገር ጥሪ ቀረበ።

10/04/2016 ለዓለም አሰፋ መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር ይነጋገር ሲል ክራይሲስ ግሩፕ ጥሪ አቀረበ። በምዕራብ ሀገራት ባሉ ፖሊሲ አውጭዎች ተደማጭነት  ያለው የሀሳብ አመንጭ ተቋም ክራይሲስ ግሩፕ የአማራ ክልል ግጭት በአፋጣኝ መፍትሔ የማያገኝ ከሆነ ለሀገሪቷ አደገኛ ይሆናል ብሏል። ተቋሙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ነፍጥ ካነገቡ የክልሉ ታጣቂዎች ጋር እንዲደራደሩ ምክር ለግሷል። መቀመጫውን በቤልጂየሟ መዲና ብራስልስ ያደረገዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ይህ ተቋም በዓለም ዙርያ ያሉ ቀውሶችን በመመርመር ትንታኔዎችን ያቀርባል፤ በመንግስታት ፖሊሲ አርቃቂዎች፥ በምሁራን እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ትንታኔዎቹ ተደማጭነት አላቸው። ድርጅቱ የአማራ ክልል ግጭትን አስመልክቶ ባወጣዉ  መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሦስቱ ክልሎች በኦሮሚያ፥ በትግራይ እና አሁን ደግሞ በአማራ መንግስትን የሚቃወሙ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የበረሃ አንበጣና ድንበር ተሻጋሪ ተባዮች ስጋት ናቸው ተብሏል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የበረሃ አንበጣና ድንበር ተሻጋሪ ተባዮች ስጋት ናቸው ተብሏል።

ይህ ይፋ የተደረገው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC ከኢጋድ አባለ ሀገራት ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በሰጠው ስልጠና ላይ ነው። ስልጠናው በዋናነት የበረሃ አንበጣና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ፀረ ሰብል ተባዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተለይ  ባለፉት አራት አመታት በቀጠናው ክፉኛ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዕከሉ ሪፓርት አመላክቷል። በጎረቤት ኬንያ ምዕራባዊ ክፍል በተገባደደው የፈረንጆቹ 2023 ብቻ 5.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት እህል በወፎች ወድሟል። ይህም በቶን ሲሰላ 60ቶን ገደማ ነው ተብሏል። በወፎች ከሚጠቁ የሰብል አይነቶች ውስጥ ማሽላ፣ስንዴ፣ሩዝ ጤፍ እና ገብስ በግባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።የሙቀት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ለተባዮች መፈልፈል እና መራባት…
ተጨማሪ ያንብቡ

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የበረሃ አንበጣና ድንበር ተሻጋሪ ተባዮች ስጋት ናቸው ተብሏል።

03/2016 በተለይ ባለፉት አራት አመታት በቀጠናው ክፉኛ የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዕከሉ ሪፓርት አመላክቷል። በጎረቤት ኬንያ ምዕራባዊ ክፍል በተገባደደው የፈረንጆቹ 2023 ብቻ 5.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት እህል በወፎች ወድሟል። ይህም በቶን ሲሰላ 60ቶን ገደማ ነው ተብሏል። ይህ ይፋ የተደረገው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC ከኢጋድ አባለ ሀገራት ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በሰጠው ስልጠና ላይ ነው። ስልጠናው በዋናነት የበረሃ አንበጣና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ፀረ ሰብል ተባዮች ላይ ያተኮረ ነው። በወፎች ከሚጠቁ የሰብል አይነቶች ውስጥ ማሽላ፣ስንዴ፣ሩዝ ጤፍ እና ገብስ በግባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።የሙቀት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ለተባዮች መፈልፈል እና…
ተጨማሪ ያንብቡ
በትላንትናው ዕለት ከሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትስር ዴኤታነታቸው የተነሱትአቶታዬደንደአ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታናደህንነት የጋራ ግብረኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

በትላንትናው ዕለት ከሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትስር ዴኤታነታቸው የተነሱትአቶታዬደንደአ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታናደህንነት የጋራ ግብረኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ታህሳስ02/2016 ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት አቶ ታዬ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተጻፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ትላንት ሰኞ ታህሳስ 1፤ 2016 ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ሚኒስትር ዴኤታው ከስልጣናቸው የተነሱበትን ምክንያት ባይጠቅስም፤ ይህንኑ ተከትሎ አቶ ታዬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባወጡት ጹሁፍ ግን ከስልጣናቸውን የተነሱት “የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገናቸው” መሆኑን አስፍረው ነበር።  የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ በዛሬው መግለጫው፤ አቶ ታዬ በተመደቡበት ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ሆነው መንግስትን “ገዳይ እና ጨፍጫፊ” እያሉ “በተደጋጋሚ ሲወቅሱ” መደመጣቸውን ጠቅሷል። ሆኖም በተግባር “ከሽብርተኞች፣ ጽንፈኞች እና ነፍሰ ገዳዮች ጋር” በተግባር “የጥፋት ትስስር የነበራቸው” ራሳቸው አቶ ታዬ መሆናቸውን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያን የማዳን መድረክ በሚል ስያሜ የተሰባሰቡ እና በውጭ ሃገራት  በተለያየ ዘርፍ የሚያገለግሉ ምሁራን ኢትዮጵያ ከገባችበት ፖለቲካዊና ሀገራዊ ቀውስ ሊታደጋት ይችላል  ያሉትን መፍትሄ የያዘ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተው  የተለያዩ አካላትን ለውይይት ጋብዘዋል፡፡

ኢትዮጵያን የማዳን መድረክ በሚል ስያሜ የተሰባሰቡ እና በውጭ ሃገራት  በተለያየ ዘርፍ የሚያገለግሉ ምሁራን ኢትዮጵያ ከገባችበት ፖለቲካዊና ሀገራዊ ቀውስ ሊታደጋት ይችላል  ያሉትን መፍትሄ የያዘ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተው  የተለያዩ አካላትን ለውይይት ጋብዘዋል፡፡

በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት የሚኖሩት እኒህ ምሁራን የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ እና ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ከእጇ ያመለጡ የዲሞክራሲ የሽግግር አማራጮችን በማሳየት አሁንም መንግስትን ጨምሮ  በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ሃይሎች ተቀራርበው ካልተነጋገሩ እና ካልተወያዩ ተመሳሳይ የታሪክ ኪሳራ ላይ እንወድቃለን ብለዋል፡፡ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በማጤን እና በመመርመር ስድስት የይሆናል አማራጮችን ያቀረበው ሰነዱ ለመንግሰት አስፈፃሚዎችም እንደደረሰ የጥናት ቡድኑ አስተባባሪዎች ትናንት በሃገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ሰምተናል፡፡ በዚህ ሰነድ ዙሪያ የመንግስት አስፈጻሚያንንን ጨምሮ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የመገናኛብዙኃን ባለሞያዎች እና ስለሃገር ግድ የሚላቸው ሁሉ እንዲወያዩ እና እንዲመካካሩ ያቀረብነውን አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብም እንዲመለከቱት እንጋብዛለን ብለዋል፡፡ save-Ethiopia-Road-Map-2Download
ተጨማሪ ያንብቡ
“በግጭቱ እየደረሰ ያለው እጅግ አሠቃቂ ጉዳት ከዚህ የበለጠ ከመባባሱ እና የበለጠ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሔ ይሰጠው ” ኢሰመኮ

“በግጭቱ እየደረሰ ያለው እጅግ አሠቃቂ ጉዳት ከዚህ የበለጠ ከመባባሱ እና የበለጠ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሔ ይሰጠው ” ኢሰመኮ

አሸናፊ አሰበ 27/03/2016 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ፤ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ ኦዳ ብልድግሉ ወረዳ፤ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣ ሸርካ ወረዳ እና በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ ኦዳ ብልድግሉ ወረዳ ሥር በሚገኙ ቤልሚሊ፣ አልከሻፊ እና ቤላደሩ ቀበሌዎች በሚኖሩ የቤኒሻንጉል ብሔር ተወላጆች እና አብረው በሚኖሩት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ…
ተጨማሪ ያንብቡ
በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል ‘የአየር ንብረት ፈንድ’ እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል ‘የአየር ንብረት ፈንድ’ እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ተደረሰ።

ህዳር 22/2016 የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝዳንት ዶክተር  ሱልጣን ቢን አህመድ አልጃብር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የበለጠ ተጎጂ ለሆኑ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። የአረብ ኢምሬትስ አመራር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ሀገራት እንዲረዱ በማድረግ አለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ጥረቶች እንዲጠናከሩ እየሰራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ዶክተር  ሱልጣን ቢን አህመድ አልጃብር ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለማሳካት ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት እና ማህበረሰቦች እንዲረዱ በተነሳሽነት ብዙ እርምጃዎችን መወሰዳቸውን ተናግረዋል። የኢምሬትስ ዜና አገልግሎት(ዋም) እንደዘገበው ዶክተር አልጃብር ይህን ያሉት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ በማደግ…
ተጨማሪ ያንብቡ
“ተቆርቋሪ ያጣው የንጹሃን ደም በአርያም ይጮሃል” እናት ፓርቲ

“ተቆርቋሪ ያጣው የንጹሃን ደም በአርያም ይጮሃል” እናት ፓርቲ

ህዳር 20/2016 ዓ.ም “ተቆርቋሪ ያጣው የንጹሃን ደም በአርያም ይጮሃል” ሲል በሰጠው ርዕስ እናት ፓርቲ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል። ፓርቲው በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ በሶሌ መድኃኔዓለም እና ሴሮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኅዳር 13 ቀን 2016 በተፈጸመ ጅምላ ጭፍጨፋ 27 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ንጹሐን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች መረዳቱን ገልጿል። “ይኼው ጥቃት ቀጥሎ ኅዳር 17 ቀን 2016 ደግሞ ስምንት ሰዎች በተመሳሳይ መልኩ ሲገደሉ በድምሩ 35 የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ንጹሐን ዜጎች መገደላቸውን አረጋግጫለው” በማለት ፓርቲው አክሏል። በርካቶችም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጸው ፓርቲው በዚህ ጥቃት ነፍሰጡር ሴትን…
ተጨማሪ ያንብቡ