በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት የሚኖሩት እኒህ ምሁራን የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ እና ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ከእጇ ያመለጡ የዲሞክራሲ የሽግግር አማራጮችን በማሳየት አሁንም መንግስትን ጨምሮ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ሃይሎች ተቀራርበው ካልተነጋገሩ እና ካልተወያዩ ተመሳሳይ የታሪክ ኪሳራ ላይ እንወድቃለን ብለዋል፡፡
ተጨባጭ ሁኔታዎችን በማጤን እና በመመርመር ስድስት የይሆናል አማራጮችን ያቀረበው ሰነዱ ለመንግሰት አስፈፃሚዎችም እንደደረሰ የጥናት ቡድኑ አስተባባሪዎች ትናንት በሃገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ሰምተናል፡፡
በዚህ ሰነድ ዙሪያ የመንግስት አስፈጻሚያንንን ጨምሮ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የመገናኛብዙኃን ባለሞያዎች እና ስለሃገር ግድ የሚላቸው ሁሉ እንዲወያዩ እና እንዲመካካሩ ያቀረብነውን አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብም እንዲመለከቱት እንጋብዛለን ብለዋል፡፡
