የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል ሲል የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ እንደ አገልግሎቱ መረጃ የህዳር ወር የዋጋ ግሽበት 28.3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች(food items) 30 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 26 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል፡፡
በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በጥቅምት ወር ከነበረበት 29.2 በመቶ ወደ 28.3 በመቶ መቀነሱን መረጃው ያሳያል ማለቱን ከአገልግሎቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክተናል፡፡
