በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ
የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው የራያ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ ወረዳ “የህወሓት ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት” ከቅዳሜ እስከ ዛሬ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ሲናገሩ፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን በበኩሉ ግጭት የተፈጠረው ታጣቂዎች በትግራይ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን ገልጿል። ከየካቲት ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገባቸው ካሉት የራያ ወረዳዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ የተከስ ልውውጡ በድጋሚ ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው እና የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ “የህወሓት ኃይሎች” በማለት የሚጠሯቸው ታጣቂዎች፤ ተኩስ የከፈቱት በወረዳው አዲስ…
