መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር እንዲነጋገር ጥሪ ቀረበ።
10/04/2016 ለዓለም አሰፋ መንግስት ከፋኖ መሪዎች ጋር ይነጋገር ሲል ክራይሲስ ግሩፕ ጥሪ አቀረበ። በምዕራብ ሀገራት ባሉ ፖሊሲ አውጭዎች ተደማጭነት ያለው የሀሳብ አመንጭ ተቋም ክራይሲስ ግሩፕ የአማራ ክልል ግጭት በአፋጣኝ መፍትሔ የማያገኝ ከሆነ ለሀገሪቷ አደገኛ ይሆናል ብሏል። ተቋሙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ነፍጥ ካነገቡ የክልሉ ታጣቂዎች ጋር እንዲደራደሩ ምክር ለግሷል። መቀመጫውን በቤልጂየሟ መዲና ብራስልስ ያደረገዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ይህ ተቋም በዓለም ዙርያ ያሉ ቀውሶችን በመመርመር ትንታኔዎችን ያቀርባል፤ በመንግስታት ፖሊሲ አርቃቂዎች፥ በምሁራን እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ትንታኔዎቹ ተደማጭነት አላቸው። ድርጅቱ የአማራ ክልል ግጭትን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሦስቱ ክልሎች በኦሮሚያ፥ በትግራይ እና አሁን ደግሞ በአማራ መንግስትን የሚቃወሙ…
