ሀገርኛ

በክልሉ የቀጠለው ግጭት ፈተና እንደሆነባቸው የአማራ ተማሪዎች ገለጹ

በክልሉ የቀጠለው ግጭት ፈተና እንደሆነባቸው የአማራ ተማሪዎች ገለጹ

ጥቅምት 10/2016 በአማራ ክልል ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ በመጣው ግጭት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በመስተጓጎሉ በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደየሚማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መመለስ እንዳልቻሉ ተናገሩ፡፡ በሲዳማ ክልል በሚገኘው ሀዋሳ እንዲሁም በዲላ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ የገለጹት ተማሪዎች፣ ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባም ኾነ የአውሮፕላን በረራ ወዳለባቸው ከተሞች ለመሔድ እንደተቸገሩ ለቪኦኤ የዜና ማሰራጫ ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ፣ ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ሦስት እጥፍ በኾነ ወጪ ከአካባቢዎቹ በአውሮፕላን ለመውጣት እንደተገደዱ ጠቅሰው፣ መንግሥት ወደየሚማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች በበኩላቸው፣ የዐማራ ክልል ተማሪዎቻቸውን በከፊል እየተቀበሉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ፣ “ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው፤…
ተጨማሪ ያንብቡ
መከላከያ በ“ሸኔ ቡድን” ላይ ወሰድኩት ባለው እርምጃ ዋና አመራሩን ገድያለሁ አለ

መከላከያ በ“ሸኔ ቡድን” ላይ ወሰድኩት ባለው እርምጃ ዋና አመራሩን ገድያለሁ አለ

ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም   በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንግስት “ሸኔ” ብሎ በሚጠራው ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑ ከፍተኛ አመራር የሆነው ጃል ቦሩ አምቦን እና ሌሎች በርካታ የቡድኑ አባላትን መግደሉን አስታወቀ። መከላከያ ሰራዊቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባሰፈረው ሀተታ በአካባቢው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባላት በምዕራብ ሽዋ ዞን በአቡና ግንደ በረት ወረዳ ፋጅና ጌርጌራ በተባሉ አካባቢዎች ላይ ጥቃት የሰነዘረው ታጣቂ ቡድንን መደምሰሱን አስታውቋል። መከላከያ በዚህ መግለጫው ቡድኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሻምበል እንግዳሸት መከተን ጠቅሶ መረጃውን አስፍሯል። በተመሳሳይ በጀልዱ ወረዳ በጩልቄ እና በሽኩቴ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ካቻ “የግልየክፍያሰነድአዉጪ” በመሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ

ካቻ “የግልየክፍያሰነድአዉጪ” በመሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2016 በኢትዮጵያ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት ላይ የተሰማራው ካቻ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት አክሲዮን ማሕበር፤ በአገሪቱ የመጀመሪያው "የግል የክፍያ ሰነድ አዉጪ" በመሆን በሙሉ አቅሙ ሥራ መጀመሩን ትናንት ሐሙስ ምሽት ጥቅምት 8/2016 በስካይላይት ሆቴል በነበረው መርሃ ግብር ላይ አብስሯል። በዚህም መሰረት የሞባይል የገንዘብ ዝውውር አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ሰነዶችን ለማውጣት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ የመጀመርያው የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ መሆን ችሏል። ካቻ ከአለም አቀፍ ሐዋላ አስተላላፊዎች ጋር በፈጠረው አጋርነት ደህንነቱ የተጠበቀ የውጪ ሐዋላን በማሳለጥ፤ ላኪዎችም ሆኑ ተቀባዮች ተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎቶች ዕድል የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጿል። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአሰራር ስርዓት ዓለም አቀፍ የሐዋላ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሥራ አጥነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ችግር እንደሆነ መንግሥት አመነ

ሥራ አጥነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ችግር እንደሆነ መንግሥት አመነ

ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 በኢትዮጵያ፣ ሥራ አጥነት እጅግ አሳሳቢ ብሔራዊ ችግር ከኾነበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በአዲስ አበባ የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የሥራ ዐውደ ርእይ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር፣ ሥራ አጥነት የችግሮች ሁሉ አውራ እንደኾነ ገልጸው፣ መፍትሔው የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል። ባሳለፍነው ረቡዕ የተከፈተው ዐውደ ርእይ፣ ከ20ሺሕ በላይ አዲስ ተመራቂ ሥራ ፈላጊዎችንና 200 ቀጣሪ ድርጅቶችን እንደሚያገናኝ ተነግሮለታል። ልዩ ልዩ አካላት በትብብር እንዳዘጋጁት የተነገረለት ይኸው ሀገር አቀፍ የሥራ ዐውደ ርእይ፣ ለስድስት ሺሕ አዲስ ተመራቂዎች፣ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተመልክቷል፡፡ በዝግጅቱ የተሳተፈው ዳሽን ባንክ፣ በሁለት ቀኑ የሥራ ዐውደ ርእይ፣ ሦስት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ቦሌ የሚገኘው ፉድ ዞን ሬስቶራንት የእሳት አደጋ ደረሰበት

ቦሌ የሚገኘው ፉድ ዞን ሬስቶራንት የእሳት አደጋ ደረሰበት

አርብ ጥቅምት 09/2016 በአሸናፊ አሰበ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ6 ልዩ ስሙ ብራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ፉድ ዞን ሬስቶራንት ሀሙስ ምሽት 4 ሰዓት ከ40 ላይ ኩሽና ውስጥ ከመጥበሻ ላይ ተነሳ በተባለ እሳት ጉዳት እንደደረሰበት የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዲስ ጊዜ ገልጸዋል፡፡ በአደጋው ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን 1 ሰዓት 30 በፈጀ ርብርብ እሳቱን ወደሌላ ቦታ ሳይዛመት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ውስጥ ለማዋል መቻሉን ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ አደጋውን ለመቆጣጠር 25 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና 4 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት…
ተጨማሪ ያንብቡ
በጎጃም ቡሬ ከተማ አቅራቢያ ግጭት መኖሩ ተነገረ

በጎጃም ቡሬ ከተማ አቅራቢያ ግጭት መኖሩ ተነገረ

ሐሙስ ጥቅምት 08/2016 ካለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል እየሰፋ የመጣው ግጭት በተለይ በጎጃም አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉን አዲስ ጊዜ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ አንፃራዊ ሰላም ካለባቸው ከተሞች ውጭ በመከላከያ ሰራዊቱ እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል ያለው ግጭት አሁንም በበርካታ የገጠር ቀበሌዎች መኖሩን እኚሁ ነዋሪዎች አረጋግጠውልናል፡፡ ሰዓት እየጠበቁ የሚሰሙት የከባድ መሳሪያ የተኩስ ድምፆች የረጋ ሕይወት  እንዳይኖራቸው ምክንያት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ምስክርነታቸውን ለአዲስ ጊዜ የሰጡት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ "ቡሬ ከተማ ላይ ጊዜያዊ ሰላም ቢኖርም ትናንት ከከተማው በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኝ ሸንዲ ከተማ አጠገብ ካለው ሰባ አዳር የሚባል አካባቢ ዙርያ ከባድ የተኩስ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሾኔ ሆስፒታል በስራ ማቆም አድማ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋረጠ

የሾኔ ሆስፒታል በስራ ማቆም አድማ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቋረጠ

ሐሙስ 08/2016 በሀዲያ ዞን በምትገኘው ሾኔ ከተማ ውስጥ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ስራ ማቋረጡን ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ላለፉት ሶስት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም ያሉ ሰራተኞች ባነሱት የስራ ማቆም አድማ መነሻነት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ተድላ አካሉ በሾኔ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ይህ ሆስፒታል ስራ ማቆሙን አምነው አገልግሎት መስጠት ካቆመ አንድ ሳምንት ማስቆጠሩን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ ይህን የዶክተር ተድላ ሀሳብ የተጋሩት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ተሰማ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ግን እንደተቆጠቡ ቪኦኤ የዜና ማሰራጫ በዘገባው አብራርቷል፡፡ ይህ አጋጣሚ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ የሚናገሩትና በባለሞያነት ሲያገለግሉ የቆዩት የተቋሙ ሰራተኞች፣ ከዚህ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የ12ኛ ክፍል ውጤት እኛንም አስገርሞናል-ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ12ኛ ክፍል ውጤት እኛንም አስገርሞናል-ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ጥቅምት 07/2016 የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ዶር) ዛሬ በርላማ ተገኝተው ከሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ለሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን የሚመለከተው ይገኝበታል። የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች በንባብ ያሰሙት የፓርላማ አባል “በተከታታይ ለሁለት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት በጣም ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ትምህርት ሚኒስቴር የፈተናውን ውጤት እንዴት ያየዋል?” ሲሉ ጠይቀዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “የ12ኛ ክፍል ውጤት እንደዚህ መሆን ሁላችንንም አስገርሞናል” ብለዋል። “የፈተናውን አሰጣጥ መቀየር ብቻ ይሄን ካሳየ፤ ከዚህ ተነስተን ብቸኛ ነገር ልንል የምንችለው፤ ከዚያ በፊት ስንሰጣቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሰላም እጦት ለሱሰኛ ቁጥር መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተባለ

የሰላም እጦት ለሱሰኛ ቁጥር መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ተባለ

ጥቅምት 07/2016 በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የሰላም እጦት እና የስራ አጥነት ቁጥር መጨመር በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ለመጣው የሱስ ተጠቂዎች ቁጥር ሚናው የጎላ እንደሆነ በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት አስራት ጫካ ለአዲስ ጊዜተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ለሚሊዮኖች መፈናቀል እና ሞት ምክንያት ሲሆን፣ ቁጥራቸው የማይገመት ህጻናትንም ቤተሰብ አልባ አድርጓል፡፡ በኢትዮጵያ ከ 5.5 ሚሊየን የሚልቁ ህጻናት ወላጅ አልባ እንደሆኑ የዩኒሴፍ ዘገባ የሚያመላክት ሲሆን ይህም ህጻናቱን ለሱስ የሚኖራቸውን ተጋላጭነት ከፍ እንደሚያደርገው ይታመናል። ጦርነት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ መፈናቀል እና ድርቅ ለሱስ አጋላጭነት ቀላል የማይባል ሚና እንደሚጫወቱ ሱስ ላይ የተሰሩ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ያስረዳሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሰፊ ሽፋን…
ተጨማሪ ያንብቡ
ከሱዳን 38ሺህ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለፀ

ከሱዳን 38ሺህ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለፀ

ጥቅምት 07/2016 በሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎችን ግጭት በመሸሽ 38ሺህ 560 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ድንበር አቋርጠው ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን አለምዓቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ፡፡ ስድስተኛ ወሩን ከተሻገረው እጅግ ደም አፋሳሽ ከሆነው ከዚህ ጦርነት ራሳቸውን ለማዳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አጠቃላይ ስደተኞች ቁጥር 85ሺህ 600 መሻገሩን ድርጅቱ ያወጣው ዝርዝር መግለጫ ያመለክታል፡፡ ከዚህ መካከል 30ሺህ 560 ያህሉ ኢትዮጵያን ሲሆኑ 31ሺህ 115 የሚሆኑት ደግሞ ሱዳናውያን ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡ የተቀሩት 15ሺህ 821ዱ ደግሞ የሶስተኛ ሀገራት ዜጎች ናቸው፡፡ ከፊሎቹ ወደ ሌሎች ሀገራት መሻገራቸውን የፍልሰተኞች ድርጅት መረጃ ጠቁሟል:: አጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ከ85ሺህ በላይ ስደተኞች መካከል 35ሺህ 440 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 50ሺህ 56…
ተጨማሪ ያንብቡ