ሀገርኛ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ

ሰኞ ጥቅምት 26 / 2016 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰይመዋል። የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል። በዚሁ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰየሙ የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ አባላት፡- 1.  ቀሲስ ታጋይ ታደለ…………….. ሰብሳቢ 2.  ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ………….አባል 3.  ባዩህ በዛብህ…………. አባል 4.  ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) …………. አባል 5.  ካሳሁን ፎሎ…………. አባል 6.  ርግበ ገብረሃዋርያ…………. አባል 7.  እንግዳዬ እሸቴ…………. አባል 8.  መላኩ እዘዘው (ኢ/ር) ………….…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭቱን ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ተነገረ።

ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭቱን ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ተነገረ።

ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2016 በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት ከፊታችን አርብ ጥቅምት 23/2016 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡ በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ መስፍን አሰፋ፤ የሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት የፊታችን አርብ ዳግም እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የአንድ ዳቦ ዋጋ 5፡00 ብር መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው፤ በአቅርቦት ረገድም በኹሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚያመርተው ድርጅቱ በተለይ ከስንዴ አቅርቦትና ግዢ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ክፍተት ምርቱ በመዲናዋ ማሰራጨት ካቆመ ከስድስት ወራት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለመዲናዋ ከ465 ሺህ በላይ ሰራዊት መቋቁሙን ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለመዲናዋ ከ465 ሺህ በላይ ሰራዊት መቋቁሙን ይፋ አደረገ።

ረዕቡ ጥቅምት 21/2016 ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የበጀት አመቱን ሩብ አመት የስራ እቅድ አፈፃፀም ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ሰራዊቱ ምንም አይነት ፋይናንስ ድጋፍ እንደማይደረግለት እና በነጻ የሚሰራ ሰራዊት መሆኑን በከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዋ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ኃብት ጉባዔ በመጭው ሕዳር ወር በኢትዮጵያ ይካሄዳል

የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ኃብት ጉባዔ በመጭው ሕዳር ወር በኢትዮጵያ ይካሄዳል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የሚያሰናዳው የ2023 የአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ጉባዔ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተነገረ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጭው ሕዳር ወር የሚከናወነው የአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ጉባዔ በአካል እና በድረ ገጽ በቅይጥ መልኩ እንደሚሰናዳ የገለጸ ሲሆን፤ አካላዊው መድረክ ደግሞ አዲስ አበባ በሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት አዳራሽ እንደሚካሄድ አስታውቋል። የአህጉሪቱ ትልቁ የምርምር እና የምጣኔ ሃብት መሰባሰቢያ የሆነው ይህ መድረክ የአህጉሪቱን ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተባባሪዎች እና ቁልፍ የሆኑ የመንግሥት እና የግልም ኩባንያዎች ወኪሎች እንዲሁም እውቅና ጀማሪ ተመራማሪዎችን ያሳትፉበታል ተብሏል። ጉባዔው መከናወን የጀመረው በግሪጎሪያን አቆጣጠር በ2006 ሲሆን፤ በዚህ ዓመት በዘላቂ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተነግሯል።
ተጨማሪ ያንብቡ
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ፡፡

 በ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡- 1. 1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል። 2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ 3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሰላም እጦት ግብር የመሰብሰቡን ስራ አዳጋች አድርጎታል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ

የሰላም እጦት ግብር የመሰብሰቡን ስራ አዳጋች አድርጎታል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ

ጥቅምት 20/2016  የአማራ ክልላዊ መንግስት በዘንድሮ በጀት ዓመት 71 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በሩብ ዓመቱ መሰብሰብ የቻለው 6 ቢሊዮን 264 ሚሊየን ብቻ መሆኑን አስታወቀ። አብዛኛዎቹ የክልሉ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚጠበቅባቸውን ገቢ በመሰብሰብ ረገድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ገቢ ከሌለ የህክምና ተቋማት እና ት/ቤቶች ይዘጋሉ፤ የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ይቆማል፤ ልማት፣ እድገት፣ ብልጽግና አይኖርም ሲሉ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ደጀኔ መናገራቸውን መረጃው አካቷል። በ2016 በጀት ዓመት 71 ነጥብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጎጎትበፓርቲው አመራር አቶመላኩሳህሌላይየተፈፀመውን እገታበማውገዝ መግለጫ አወጣ፡፡

ጎጎትበፓርቲው አመራር አቶመላኩሳህሌላይየተፈፀመውን እገታበማውገዝ መግለጫ አወጣ፡፡

የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መላኩ ሳህሌ በቀን 14/02/2016 ዓ.ም ከቤታቸው አቅራቢያ ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል ያለው ፓርቲው ጥቅምት 16 አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት አቶ መላኩ ሳህሌ ፖሊስ "ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር እና ከጠላት ጋር በማበር" የሚል  ክስ ቢያቀርብባቸውም ችሎቱ በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ብሏል። በዚሁ መሰረት የዋስትና ብር ተከፍሎ አቶ መላኩ ከፖሊስ ጣቢያ ይወጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፖሊስ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አዛውሮአቸው እስካሁኑ ሰአት ድረስ በእገታ ላይ ይገኛሉ ያለው መግለጫው ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ የተፈቀደላቸውን…
ተጨማሪ ያንብቡ
የአየር ንብረት ለውጥ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ

የአየር ንብረት ለውጥ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ

በዘላቂ የልማት ግቦች እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚያጠነጥን የግማሽ ቀን አውደ-ጥናት ትናንት ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱን አዲስ ጊዜ አይታለች፡፡ ኤንዳ ኢትዮጵያ በመባል በሚታወቀው እና በዋናነት በከተማ ልማት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በሚሰራው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ መርሀ-ግብር ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን በተለያዩ የዜና ማሰራጫ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሐን ባለሞያዎችም የውይይቱ አካል ነበሩ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ምልክቶች እና እያስከተሉ ያሉት መጠነ ሰፊ ጉዳቶች በአውደ-ጥናቱ ላይ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ በተለይ፣ ችግሩ ከኢትዮጵያ አንጻር የተዳሰሰበት ክፍል በተሳታፊዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንደነበር መታዘብ ተችሏል፡፡ እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ይሳካሉ ተብለው ግብ የተያዘላቸው…
ተጨማሪ ያንብቡ
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን የጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን የጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

ጊዜአዊ ኮማንድ ፖስቱ "በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና በአካባቢው አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መሻሻል እየመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ መልኩ ማከናወን እንዲችል የሰው፣ የባጃጅና ሆቴሎች  የስራ ሰዓት ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።" ሲል ገልፆል። በዚህም መሠረት ከዛሬ ጥቅምት 21/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ መንቀሳቀስ የሚቻለው ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አሳውቋል።  ከዚህ ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ በሚያደርግ ማንኛውም አካል  ላይ ኮማንድ ፖስቱ  በሚወስደው ህጋዊ እርምጃ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን አክሎ አሳውቋል፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከወልቂጤ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሥራዉን በይፋ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሥራዉን በይፋ ጀመረ።

ኮሚሽኑ በክልሉ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን   አስመልክቶ በሆሳዕና ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ  ኮሚሽነር  ዶክተር ዮናስ አዳዬ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለኮሚሽኑ ከወዲሁ እያሳየ ላለዉ ትብብር አመስግነዉ ይህም ለኮሚሽኑ አዎንታዊ ዉጤት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በበኩላቸው ኮሚሸኑ የተቋቋመበትን ህጋዊ መሠረት ጠቅሰዉ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከነገ ጀምሮ  በሆሳዕና ከተማ ለተባባሪ አካላት ሥልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። ለሦሥት ተከታታይ ቀናት በሚቆየዉ ሥልጠና ከተለያዩ ማኅበራዊ መሠረት የተዉጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሥልጠናዉ የምክክር ጽንሰ-ሀሳብ፣ አላማ፣ ሂደት፣ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች የተመለከቱ   ርዕሰ-ጉዳዮች ይቀርባሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር  1265/2014 ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል።  መረጃዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሚንኬሽን…
ተጨማሪ ያንብቡ