መንግስት በፈፀማቸው የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ባወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት መንግስት ታህሳስ እና ግንቦት ላይ በፈጸማቸው ሁለት የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቆስለዋል ብሏል ፡፡ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እጅግ አሳሳቢ ሆነው የቀጠሉ የመብት ጥሰቶች መሆናቸው ተገልጿል። ኮሚሽኑ በጸጥታ ችግር እና ከመንግስት ተገቢውን ትብብር ባለማግኘት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የዘገዩ ምርመራዎች በሂደት…
