ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰየሙ
ሰኞ ጥቅምት 26 / 2016 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰይመዋል። የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል። በዚሁ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰየሙ የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ አባላት፡- 1. ቀሲስ ታጋይ ታደለ…………….. ሰብሳቢ 2. ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ………….አባል 3. ባዩህ በዛብህ…………. አባል 4. ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) …………. አባል 5. ካሳሁን ፎሎ…………. አባል 6. ርግበ ገብረሃዋርያ…………. አባል 7. እንግዳዬ እሸቴ…………. አባል 8. መላኩ እዘዘው (ኢ/ር) ………….…
