አዲስ ጊዜ

227 Posts
በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በመወከል በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27፣ 2017 በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የርክክብ ስነ ስርዓት፤ ፤ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “ሊመከርባቸው ይገባሉ” ብለው የመረጧቸውን ጉዳዮች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት አስረከቡ። ተወካዮቹ አጀንዳዎቻቸውን በስምንት ርዕሰ ጉዳዮች በመከፋፈል  ያቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና አወቃቀር፣ ቋንቋ፣  ታሪክ እና ትርክት፣ የሃገረ መንግስት ግንባታ እና የሃገር አንድነትን፣ የአንድነት እና ብዝሃነትን የሰንደቅ አላማ እና የህገ መንግስት ጉዳዮችን የተመለከቱ ይገኙበታል ተብሏል። አሁን በስራ ላይ ካለውን የኢፌዲሪ ህገ መንግስት…
ተጨማሪ ያንብቡ
መንግስት በፈፀማቸው  የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

መንግስት በፈፀማቸው  የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ባወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት መንግስት ታህሳስ እና ግንቦት ላይ በፈጸማቸው ሁለት የድሮን ጥቃቶች 10 ሰዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቆስለዋል ብሏል ፡፡ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፣ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እጅግ አሳሳቢ ሆነው የቀጠሉ የመብት ጥሰቶች መሆናቸው ተገልጿል። ኮሚሽኑ በጸጥታ ችግር እና ከመንግስት ተገቢውን ትብብር ባለማግኘት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የዘገዩ ምርመራዎች በሂደት…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

ኢትዮጵያ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደምታስተናግድ ኢጋድ ተነበየ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና ትግበራ ማዕከል ICPAC በቀጣይ አራት ወራት ማለትም ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 2017 ዓ.ም  ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የሚኖረውን የዝናብ እና መጠነ ሙቀት ሁኔታ ትንበያ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ክረምት በምንለው እና በሰሜኑ የምስራቅ አፍሪካ ክፍል በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ጁቡቲ፣ኤርትሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ዮጋንዳና ምዕራብ ኬንያን ጨምሮ በቀጣይ አራት ወራት ከመደበኛው ዝናብ በላይ እንደሚያገኙ የማዕከሉ ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ሁሴን ሰዒድ ተናግረዋል። ሁሴን አክለው በተለይ ለምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ፣ሰሜን፣ሰሜን ምስራቅ፣መካከለኛ የኢትዮጲያ ክፍል መጪው የክረምት በጣም ወሳኝ ወቅት ስለሆነ  ከፍተኛ ኤና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ያስተናግዳሉ። በመሆኑም…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመንግስት ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መንግስት ከፍተኛ ጥቃትና ጫና እየፈጸመበት እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡ ኢሰመጎ በመግለጫው በመንግስት እየደረሰበት ያለው ጥቃት እና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን  አሳውቋል። ጉባኤው በተለያዩ ጊዜ ተፈጽመውብኛል ያላቸው ጥቃቶች እና ከፍተኛ ጫናዎች በመግለጫው ላይ የዘረዘረ ሲሆን በተቋሙ አመራር ላይ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የሚፈጸም ክትትል ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየጨመረ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ክትትል ስራችሁን ካላቆማችሁ ፤ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት መወንጀል ካላቆማችሁ  ‘ ዋጋ ትከፍላላችሁ ‘ የሚል ዛቻ እየደረሰበት መሆኑን ገልጿል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የመንግስት ጸጥታ አካላት አካላዊ ጥቃት ማድረስ፣ መሳደብ፣ ማንገላታት፣ ስራቸውን እንዲያቆሙ ማስፈራራት…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኪነጥበብ ስራዎችን ማገድ ሃሳብን በነፃነት መግለጽ መብትን ማገድ ነው-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  

የኪነጥበብ ስራዎችን ማገድ ሃሳብን በነፃነት መግለጽ መብትን ማገድ ነው-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል  ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለመስቀል   የኪነ ጥበብ ስራዎች ሀሳብን በነጻነት የመግለጫ መንገድ በመሆናቸው  ከጥቃት ሊጠበቁ እና ባለሙያዎችም ለእስር ሊዳረጉ አይገባም ብለዋል፡፡ መንግስት ለኪነ ጥበብ ሙያ እና ባለሙያዎች ልዩ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባል ያሉት አቶ ያሬድ ኪነ-ጥበብ ለሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ መዳበር፣ መጎልበት እንዲሁም  መስፋፋት እና መከበር ያለው ጉልህ ሚና እጅግ የላቀ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም የኪነ-ጥበብ መድረኮች እና ባለሞያዎች በሙዚቃ፣ በቲያትር፣ በግጥም፣ በስዕል እና በቅርፃቅርፅ መልክ የሚያንጸባርቋቸው ሃሳቦች የዜጎች ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት መገለጫዎች እንደሆኑ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። እነዚህ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ለአንድ ማህበረሰብ የደስታም ሆነ የብሶት ሃሳቦቹን የሚገልጽባቸው መንገዶች የመሆናቸውን ያህል በአገር አስተዳደር ኃላፊነት ላይ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ሌንጮ ባቲ ስለሺ በቀለን ይተካሉ?

ሌንጮ ባቲ ስለሺ በቀለን ይተካሉ?

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ   ከአምባሳደርነት ሹመታቸው እንዲሁም ከማንኛውም የመንግስት ሃላፊነት  በመልቀቅ በግል  በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውን እና ጥያቄ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ይህንን ተከትሎ አምበሳደር ስለሺ  ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮቻችን ነግረውናል። አምባሳደር ስለሺ በቀለ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው በግል ተቀጥረው ሲያገለግሉ ነበር። የቀድሞው የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ መምህር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት ከመሾማቸው በፊት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ከአምስት ዓመት በላይ አገልግለዋል፡፡ አምባሳደር ሽለሺ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…
ተጨማሪ ያንብቡ
ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ከአገር ለመሰደድ መገደዱን ተናገረ

ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋዜማ ሬዲዮ፣ ኢኤምኤስ እና ሌሎችም ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ “ሕገ ወጥ ግንባታ” ናቸው ተብለው በፈረሱ ወደ 100 ሺህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና በተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ለዘገባ ወደ ስፍራው ባመራበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በፖሊስ ድብደባ፣ እስርና ማዋከብ ደርሶበት እንደነበር የተናገረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ በዋስ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዲከራከር በፍርድ ቤት ተወስኖለት ቢወጣም ዛቻና ማስፈራሪ ሲደርስበት እንደነበረ ነግሮኛል ሲል ኢትዮ ነጋሪ አስነብቧል፡፡ በቅርቡም ለዋዜማ ሬድዮ እና ኢንተር ኒውስ ዘገባ ለመስራት ወደ አማራ ክልል ደሴና ሐይቅ ከተሞች በተጓዘበት ወቅት በክልሉ ኮማንድ ፖስት ታስሮ እንደነበረም አክሏል።…
ተጨማሪ ያንብቡ
ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

የቴሌቪዥን ባለንብረቶች ለሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል አሉ፡፡ በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የሚከለው ዋጋ ውድነት አሳስቧት ነበር አባላቱ ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ለእነዚህ የቴሌቭዥን ባለንብረቶች  ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል ብሎ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ ሰባ የሚሆኑ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች  ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ…
ተጨማሪ ያንብቡ
የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር “ሳይጠየቁ ምክር” ሰጥተዋል ሲል ወቀሰ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር “ሳይጠየቁ ምክር” ሰጥተዋል ሲል ወቀሰ

በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በቅርቡ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ያሰሙት ንግግር "በደንብ ያልተጤነ" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወቀሰ። አምባሰደር ማሲንግ ከጥቂት ቀናት በፊት "ፖሊሲ ስፒች ኦን ሂዩማን ራይትስ ኤንድ ዳያሎግ" የተሰኘ ንግግር አሰምተው ነበር። ማሲንጋ በንግግራቸው መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች እንዲቆሙ፤ ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖር እና ለዚህም መነሻ የሚሆን ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም አንዲደረግ አሳስበው ነበር። ማሲንጋ  በንግግራቸው ሽፍቶች፣ ታጣቂ ቡድኖችና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በህይወት የመኖር እና የመከባበር መብቶች ላይ ጥሰት መፈፀማቸው የሕግ ሂደትንና የሕግ የበላይነት አለማክበርን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በጦርነት እና ግጭት ጊዜም ቢሆን “የሰብዓዊ መብት እና ሰብዓዊ ክብር”…
ተጨማሪ ያንብቡ
የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ

የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የዑለማ ጉባዔ፣ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን በማስመልከት የወጣው መግለጫ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ ጥር 22 ቀን፣ 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ በቁጥር 12 እና 13 ላይ የሰፈረው ውሳኔ ከሴቶች መብት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንጻር ተቃርኖ እንዳለው እንደ “አዲስ ፓወር ሃውስ’’ እና “አርቲክል 35” ያሉ በሴቶች መብት ላይ የሚሠሩ ንቅናቄዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ድምጻቸውን እያስተጋቡ ነው። በመግለጫው ላይ በቁጥር 12 እና 13 የሰፈሩት ውሳኔዎች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል። እነዚህንና ሌሎች በመግለጫው የተካተቱ “ውሳኔዎችና ፈትዋዎችን የእስልምና ጉዳዮች…
ተጨማሪ ያንብቡ